በራስ አቅም ጥገና የቆሙ ዩኒቶችን ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉ ተገለፀ

በጊቤ 2 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ካሉት አራት ዩኒቶች መካከል በዩኒት አንድ እና በዩኒት ሦስት ላይ ሙሉ ጥገና በመደረጉ ተጨማሪ 180 ሜጋ ዋት ማግኘት መቻሉን የጣቢያው ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ገረመው ገልፀዋል። ጣቢያው በ2002 ዓ.ም ተመርቆ በይፋ ስራ የጀመረ ሲሆን እያንዳንዳቸው 105 ሜ.ዋ የማመንጨት አቅም ያላቸው አራት ዩኒቶች ያሉትና በድምሩ 420 Read more…

የአዳማ ሁለት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያና ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

የአዳማ ሁለት ባለ 230/132/15 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያና ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አስታወቀ፡፡ የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ ሽኩር እንዳስታወቁት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና የማስተላለፊያ መስመር ግንባታው 97 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፎች ተከፍሎ እየተገነባ ነው ያሉት አቶ መሐመድ Read more…

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ጥቃት የተፈፀመበት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ተዘከረ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራሮች እና ሠራተኞች ‹‹አልረሳውም! እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ›› በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ጥቃት የተፈፀመበትን አንደኛ ዓመት አስበዋል፡፡ በህዝብና በመንግሥት የተጣለባቸውን ግዳጅ ሲወጡ በጁንታው ኃይል ክህደት ለተሰው የመከላከያ ሠራዊት አባላትም የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ዘክረዋል፡፡ በዋና መስሪያ ቤት በተካሔደው መርሃ-ግብር ላይ Read more…

በጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃው ሳይፈስ ስኬታማ ጥገና ተከናወነ

በጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃው ሳይፈስ ከ18 ሜትር ጥልቀት በላይ ወደ ውሃ ውስጥ በመግባት ስኬታማ ጥገና መከናወኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ንጉሳ ገለጹ፡፡ ግድቡ ላይ 1.5 ሜትር ክበት ስንጥቅ በመኖሩ ግድቡ ውሃ የማስረግ ችግር ገጥሞት እንደነበር የገለፁት አቶ ደሳለኝ በዘመነ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ውሃው ሳይፈስ ጥገናውን በማከናውን ችግሩን መቅረፍ Read more…

ዘርፉን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ እየተሰራ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግ  የስራ  ክፍል  የስራ ዘርፉን  ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድርግ   የአቅም ግንባታ  ስራ ፕሮጀክት ቀረጾ ወደ ትግበራ መግባቱን የስራ ዘርፉ ስራ አስፈጻሚ ገለጹ፡፡ ስራ አስፈጻሚው አቶ ውድነህ የማነ እንደ ገለጹት በተቋም ድረጃ የተሰጠውን ተልዕኮ እና  የስራ ዘርፉን ከኃይል ሽያጭ በተጨማሪ በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በማድረግ  አንድ የገቢ Read more…

ተቋሙ የ2014 አንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ገመገመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ ሥራ አመራር የተቋሙን የአንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ እንቅስቃሴ ገምግሟል፡፡ ከጥቅምት 9 ጀምሮ ለሶስት ቀናት በተደተገው ግምገማ የስራ ክፍሎች በሩብ ዓመቱ ያከናወኗቸውን ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን በዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ከኦፕሬሽን ስራዎች አኳያ በኃይል ማመንጫዎች፣ ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎች በኩል የኦፕሬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ጥገና ሥራዎች በሩብ ዓመቱ የተሻለ Read more…

ጣቢያው አገልግሎቱን በብቃት፣ በጥራትና በተገቢው መንገድ እየሠጠ ነው

ከአዲስ አበባ በ319 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ክልል በሀላባ ከተማ የሚገኘው የሀላባ ባለ 230/132/15 ኪ.ቮ. ከፍተኛ ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎቱን በብቃት፣ በጥራትና በተገቢው መንገድ ኃይል  እየሠጠ ይገኛል፡፡ የጣቢያው ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም ገበየው እንደገለፁት በ1982 ዓ.ም. ከሶዶ1 በ132  ኪ.ቮ. መስመር ኃይል በመቀበል ለሀላባ እና ለአካባቢው በ15 ኪ.ቮ. ኃይል በመስጠት በይፋ ሥራ የጀመረው Read more…

ጣቢያው አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ እያሳለጠ ይገኛል

የይርጋለም2 ባለ 400/230/132/15 ኪ.ቮ. ማከፋፈያ ጣቢያ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የማከፋፈያ ጣቢያው ኃላፊ  አቶ ተስፋዬ ኢርባ ገለጹ፡፡ አቶ ተስፋዬ እንደገለጹት በ2011 ዓ.ም. በይፋ ስራ የጀመረው ጣቢያው አራት ባለ 400 ኪ.ቮ ገቢ መስመር ፣ጥንድ  ባለ 230 ኪ.ቮ.፣ሁለት ባለ 132 ኪ.ቮ. እና 3 ባለ 15 ኪ.ቮ. ወጪ መስመሮች አሉት፡፡ አራቱ ባለ 400ኪ.ቮ. Read more…

ተጨማሪ ኃይል ለማቅረብ ዝግጁ ሆነን እየጠበቅን ነው

ከአዲስ አበባ በ275 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በሲዳማ ክልል በሀዋሳ  ከተማ የሚገኘው የሀዋሳ 2 ባለ 230/132/33/15 ኪ.ቮ. ከፍተኛ ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎቱን ሳያቋርጥ እየሰጠ ይገኛል፡፡ በ2011 ዓ.ም አገልልግሎት መስጠት የጀመረው ማከፋፈያ ጣቢያው 20 ባለ 33 ኪ.ቮ. እና 8 ባለ 15 ኪቮ ወጪ መስመሮች እንዳሉት የጣቢያው ተወካይ ኃላፊ  አቶ አሸናፊ ይልማ ተናግረዋል፡፡ እንደ Read more…

ስርቆትን ለማስቀረት ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ  ሪጅን ትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ቢሮ በሪጅኑ እየተስፋፋ  የመጣውን  የታወር ብረት  እና የኬብል ስርቆት ወንጀል ለመከላከል  የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገለጻ፡፡ የቢሮው ዳይሬክተር  አቶ አለማየው  ዘበርጋ እንደተናገሩት   የታወር ብረት  እና የኬብል ስርቆት ወንጀል በሪጅኑ በተደጋጋሚ ከሚከስትባቸው አከባቢዎች መካከል የምእራብ አርሲ ዞን አንዱ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ አካባቢ ስርቆቱን Read more…