Published by corporate communication on
የERP ትግበራ ለተቋማዊ ራዕይ ስኬት
ፕሮጀክት ዓባይ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውስጥ አሰራሩን ለማዘመን ብሎም የአገልግሎት ጥራት ለመጨመር ERP የተሰኘ ሲስተም ለመተግበር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ይህ የሲስተም ትግበራ ስምምነት ፕሮጀክት ዓባይ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ፕሮጀክት ዓባይን በተሳካ ሁኔታ ለመተግበር ከሁለቱም ድርጅቶች የተወጣጣ ከ100 በላይ ሰዎች የሚያሳትፍ ቡድን ተቋቁሟል፡፡
ፕሮጀክቱ የሚያልመዉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውስጥ አሰራሩን ዓለም አቀፍ አሠራሮችን በውስጡ በያዘዉ ኤስ ኤ ፒ ኢ አር ፒ ሶፍትዌር (SAP S/4HANA) በማዘመን በውስጥ የሚሰራቸዉን ስራዎችና ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት እጅግ በላቀና ዘመናዊ በሆነ መልኩ እንዲሰራ ማስቻል ነዉ፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉትን የ SAP S/4HANA ሲስተሞች ይተገብራል፡፡
ለሠዉ ኃይል ሥራ አመራር – human capital management (SAP HCM)
ለፋይናንስና ቁጥጥር የሥራ ዘርፍ – finance and controlling (SAP FICO)
ለፕሮጀክት ሥራ አመራር – Project Systems (SAP PS)
ለንብረት አስተዳደር – Enterprise Asset Management (SAP PM)
ለሽያጭና ስርጭት – Sales and Distribution (SAP SD)
ለግዢ የሥራ ዘርፍ – Procurement and Inventory (SAP MM)
ለማኔጅመንት ሪፖርቶች (Analytics and Reporting)
ከላይ የተመለከቱትን በተሳካ ሁኔታ ለመጠቀም የሚያስችል የቴክኖሎጂ ፕላትፎርም – SAP FIORI, SAP BASIS, SAP Solution Manager የሚዘረጋ ይሆናል፡፡
የፕሮጀክት ዓባይ ትግበራ የሚከናወነዉ በሶስት ምዕራፎች ነዉ፡፡
በምዕራፍ 1 – ዋና ዋና ( መሰረታዊ) የፋይናንስ ሲስተሞች ፣ ዋና ዋና (መሰረታዊ) የሰዉ ኃይል አስተዳደር ሲስተሞች – HR (organization management (OM), personnel administration (PA), and payroll (PY))፣ ቢሊንግ ዋና ዋና መሰረታዊ የግዢ አሰተዳደር የፕሮጀክት ስራ ዘርፍ ሲስተሞች
በምዕራፍ 2 – ቀጣይ የሰዉ ኃይል አስተዳደር ሲስተሞች HR ( Time and Leave, Performance/Goal Management and Employee Self-Service/ Manager Self-Service (ESS/MSS) ) ፣ ቀጣይ የገዢ አስተዳደር እና ሌሎች ሲስተሞች Extended Procurement, Plant Maintenance (PM) / Enterprise Asset Management (EAM)/Fleet Management and WCM(Work Clearance Management), Cash and Treasury Management
በምዕራፍ 3- የማኔጅመንት ሪፖርቶች ፣ ተጨማሪ የሰዉ ኃይል አስተዳደር ሲስተሞች HR(Environment Health and Safety Management (EHSM)፣ የመጋዘን አስተዳደር ሲስተም Warehouse Management System (WMS)
እያንዳንዱ ምዕራፍ የሚከናወነዉ የሚከተሉትን ደረጃዎች ተከትሎ ነዉ፡፡
የዝግጅት ሥራዎች መስራት (preparation)፣
የዲዛይን ሥራዎች መስራት (explore/design)
ዲዛይን የተደረገዉን የመገንባት፣ የመሞከርና የመፈተሽ ስራዎች መስራት (realize/build and test)፣
የተገነባዉን ሲስተም ሥራ ላይ የማዋል ስራዎች
አስፈላጊ የሆኑ ሰርቨሮችና ሌሎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ማዘጋጀት፤
ለእያንዳንዱ ሲስተም ትግበራ የሚያስፈልገዉ መጠን ስልጠና መስጠት፤
አሁን ያሉትን የድርጅቱን አሰራሮች ለመረዳት ዉይይቶችና ወርክሾፖች ማካሄድ
ሌሎች የፕሮጀክት ድጋፍ ስራዎች ማከናወን፤
አሁን በጀመርነዉና ሁለት ወር በሚወስደዉ የምዕራፍ 1 ሁለተኛ ደረጃ፣ በመጀመሪያዉ ደረጃ የተሰራዉን ተመርኩዘን ብዙ ዉይይቶችና ወርክሾፖች በማከናወን የወደፊቱን ሲስተም ዲዛይን የማድረግ ስራ እንሰራለን፡፡ ከዚህ ደረጃ የሚገኘዉ ዉጤት የተለያዩ ሲስተሞች ዲዛይን ዝግጅት ነው፡፡
በቀጣይ እትማችን ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁ እናሳዉቃችኋለን ፡፡
ይቀጥላል………
የኢ.ኤ.ኃ. ዋና ሥራ አስፈጻሚ መልዕክት
የ ERP ሲስተም እንደ ኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል ላሉ በጣም ብዙ ሀብትን ለሚያንቀሳቅስ ተቋም
አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ለዚህም ተቋማችን የSAP HANA ERP ሲስተምን ተግባራዊ ለማድረግ ከኢትዮጲያ አየር መንገድ ጋር የትግበራውን ስራ ጀምሮ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በማጠናቀቅ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ተሻግሯል፡፡
የፕሮጀክቱ ወሳኝ ምዕራፎችን ከግብ ለማድረስ የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ንቁ ተሳትፎ እና ትኩረት ይሻል፡፡ ስለዚህ በሁሉም ዋና የስራ ሂደቶች ላይ የተፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንችል ዘንድ የማያቋርጥ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ጠንካራ የስራ አፈጻጸም ከሁሉም ዘርፍ ይጠበቃል፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ባለድርሻ አካላት እጅ ለእጅ ተያይዘን ለሲስተሞቻችን በተሳካ ሁኔታ መተግበር መረጋገጥ እንድንሰራ አደራ እላለሁ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር መልዕክት
የ ERP ትግበራ በባህሪው ሁልጊዜም የተቋምን አሠራር ትራንስፎርም የሚያደርግ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለራሱ ERP ን ተግብሮ የመጠቀምና በየጊዜውም አስፈላጊ የሆኑ ማሻሻያዎችን እያደረገ የመገልገል የ10 ዓመታት ልምድ አካብቷል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በፕሮጀክት ዓባይ ለሚተገበረው ERP ተቋማችን ያሰማራው የሠው ኃይል ለፕሮጀክቱ በሚያስፈልገው ዘርፍ ሁሉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን ኤክስፐርቶቹን ነው፡፡
ይህ ደግሞ ለድርጅቱ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችንም ትልቅ አቅም ይፈጥራል፡፡
ይህንን አቅም ተጠቅመን ፕሮጀክት ዓባይን በሚፈለገው የጥራት ደረጃ በተበጀተለት በጀት እና በተወሰነለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ አበክረን እንደምንሰራ ለማረጋገጥ እወዳለው፡፡
0 Comments