ከጀርመን መንግስት የተወጣጡ ልዑካን የረጲ ደረቅ ቆሻሻን ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጎብኙ

ከጀርመን መንግስት ፓርላማ አባላት እና ባለሃብቶች የተወጣጡ የልዑካን ቡድን አባላት የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ጎብኙ፡፡ የልዑካን ቡድኑን የተቀበሉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዳርጌ እሸቴ ናቸው፡፡ ሥራ አስፈጻሚው እንደገለፁት ጣቢያው የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ ከበካይ ጋዝ ነጻ የሆነ የቆሻሻ አወጋገድ ስርአት ለመፍጠርና የከተማውን ጽዳት ተጨማሪ ያንብቡ…

ተቋማዊ ለውጡን ለማስቀጠል የአፈፃፀም አመራር ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ተባለ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተጀመረውን ተቋማዊ ለውጥ ሥር እንዲሰድ ለማድረግ የአፈፃፀም አመራር (performance management) ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡ ተቋሙ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ አስኪያጆች በአፈፃፀም አመራር ስርዓትና በተቋሙ ስትራቴጅክ እቅድ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም መስጠት ጀምሯል፡፡ በተቋሙ የፐርፎረማንስና ሪዋርድ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተማም ተጨማሪ ያንብቡ…

የሻምቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት ግንባታን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው

ባለ 230 ኪ.ቮ የሻምቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታን በተያዘለት የጊዜ መርሀ ግብር ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚኒልክ ሠለሞን ተናገሩ፡፡ ፕሮጀክቱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ 16 ወራት እንደሚወስድ ዕቅድ ተይዞለታል፡፡ ባለፉት ሁለት ወራትም የቢሮና የመኖሪያ ቤቶች፣ የተለያዩ ዕቃዎች እና የትራንስፎርመር የመሰረት ቆፋሮ የተጠናቀቁ ሲሆን የፋውንዴሽን አርማታ ሥራ ተጨማሪ ያንብቡ…

ተቋሙን የማዘመን ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሚፈለግበት ደረጃ ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ ተቋም የማድረግ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተቋሙ የሞደርንናዜሽን ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ የጽ/ቤቱ ዳሬክተር አቶ ሐብታሙ ውቤ እንደገለጹት ተቋሙን ዘመናዊና ተወዳዳሪ ተቋም ለማድረግ በተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ እና በተቋሙ ኃላፊዎች በተሰጠው ትኩረት የሞደርንናዜሽን ጽ/ቤት ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ጽ/ቤቱ የውስጥ አሰራር (Process ተጨማሪ ያንብቡ…

ዩኒቨርሲቲው ሲጠቀምበት የነበረውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስልጠና ማዕከል

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ ሲጠቀምበት የነበረውን የስልጠና ማዕከል ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያስረክብ ውሳኔ መተላለፉን የንብረት አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ አበበ ጉዲሳ እንደገለጹት ንብረትነቱ በቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የሆነና በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞው ወረዳ 28 ቀበሌ 2 በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር ነ-196/96 ተመዝግቦ ተጨማሪ ያንብቡ…

የቅድመ ኃይል ማመንጫ ዩኒቶች የኮንክሪት ሙሌት ስራ ጀመረ

 ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ የኒቶች መካከል ቅድሚያ ኃይል የሚያመነጩት ዩኒት 9 እና የዩኒት 10 ማዕከላዊ ክፍል የስቲል ስትራክቸር ሥራዎች በማለቃቸው የኮንክሪት ሙሌት ስራ መጀመሩ በምክትል ስራ አስኪያጅ የህዳሴ ግድብ ፕሮጅክት ሳይት አስተባባሪ አቶ በላቸው ካሳ ገልፀዋል፡፡ በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩት የኤሌክትሮ ሚካኒካልና ኃይድሮ ተጨማሪ ያንብቡ…

አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማምረት በትኩረት እየሰራ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2012 በጀት ዓመት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማምረት በኦፕሬሽን፣ ጥገናና ኢንስፔክሽን ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ በተቋሙ የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዳርጌ እሸቴ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ 16,446.85 ጊጋ ዋት ሰዓት ለማምረት እቅድ ተይዟል፡፡ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት በጣቢያዎች ላይ የኦፕሬሽን.፣ ጥገናና ኢንስፔክሽን ስራዎች በእቅድ እንዲከናወኑ ተጨማሪ ያንብቡ…

የገናሌ ዳዋ IIIየኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በጥሩ ሁኔታ ውሃ በመያዝ ላይ ይገኛል

የሁለት ክረምት ባለቤት በሆነው ገናሌ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኘው የገናሌ ዳዋ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በጥሩ ሁኔታ ውሃ በመያዝ ላይ መሆኑን የፕሮጀክቱ ተወካይ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴወድሮስ ሁሴን ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የግድቡ የውሃ መጠን 88 ሜትር ከፍታ የደረሠ መሆኑን ያስታወቁት ተወካይ ሥራ አስኪያጁ የሚፈለገው ውሃ መጠን ላይ ለመድረስ ተጨማሪ ያንብቡ…

የጊቤ III የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ የውኃ መጠኑ ከፍታ ጨመረ

 የጊቤ III የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ውኃ የመያዝ አቅሙ 880.2 ሜትር ኪዩብ ከባህር ጠለል በላይ የደረሰ ሲሆን ከዓለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ19.2 ሜትር ከፍ ብሎ ይገኛል፡፡ የጊቤ III የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ሰሙ እደገለፁት ባለፈው ዓመት ግድቡ አጠቃላይ ይዞት የነበረው ውኃ 861 ሜትር ኪዩብ እንደነበር ተጨማሪ ያንብቡ…

ብቃትን መሠረት ያደረገ የሙያ ደረጃ ማሻሻያ ስርዓት ሊተገበር ነው

የኢትዮጵያን ኤሌክትሪክ ኃይል ብቃትን መሠረት ያደረገ የሙያ ደረጃ ማሻሻያ ስርዓት ሊተገብር መሆኑን አስታወቀ፡፡ በአተገባበሩ ዙሪያ ከተቋሙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተወጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ሥልጠናውን የሠጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰው ሃብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክተር ዶ/ር ወንደሰን ካሣ እንደተናገሩት አዲስ የተቀረፀውን የተቋሙ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ፣ ራዕይ እና ግቦች ለመተግበር ተጨማሪ ያንብቡ…

Facebook