የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 68 ነጥብ 3 በመቶ ደረሰ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኢንጂነር አብርሃም በላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ያለበትን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክተው በጽ/ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ 68 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል፡፡ የኮርቻ ቅርፅ ግድቡ ግንባታ 96 በመቶ መድረሱን ያስታወቁት ዋና ሥራ አስፈፃሚው በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ያንብቡ…

በተቋሙ እየተከናወኑ ባሉ የለውጥ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች እየተገኙ ነው

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ሥራዎች አበረታች ውጤት ማስመዝገባቸውን የጊቤ ሁለት የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገበየሁ በላይ ተናግረዋል፡፡ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የጊቤ ሁለት ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ከጎበኙ በኋላ በሰጡት በሳል አመራር በርካታ ችግሮች እየተፈቱ መሆኑን ነው አቶ ተጨማሪ ያንብቡ…

የተቋሙ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለፀ

ከ2012 እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋሙ የሚመራበትን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (ኢ.ኤ.ኃ) ከ2012 እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋሙ ለቀጣይ ስድስት ዓመታት የሚመራበትን ስትራቴጂ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ዝግጅትን በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ቢሮ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት አማን ገልፀዋል፡፡ ስትራቴጂን ተጨማሪ ያንብቡ…

Facebook