ጣቢያው ዩኒት ሊያስቆሙ የሚችሉ ብልሽቶችን በራስ አቅም እየጠገንኩ ነው አለ

Published by corporate communication on

የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ዩኒቶችን ሊያስቆሙ የሚችሉ ብልሽቶችን በራስ አቅም እየጠገነ መሆኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢምረው ዳኜ ገለፁ፡፡

ሥራ አስኪያጁ እንደገለፁት በዘይት የሚሰራው የውሃ መቆጣጠሪያ ቀለበት (Operating ring) የመሰንጠቅ አደጋ ገጥሞት የነበረ ቢሆንም በተቋሙ የጥገና ባለሙያዎች ሞደፊክ ተደርጎ በመስራት ተጠግኗል፡፡

በዚህም ዩኒቱ ሳይሰራ ለረጅም ጊዜ እንዳይቆም በማድረግ፣ የጥገና ባለሙያ ከውጪ ሀገር ሳይጠብቅና የውጭ ምንዛሪ ሳይወጣበት ብልሽቱን መጠገን አስችሏል፡፡

በተመሳሳይም በማቀዝቀዣ ስርዓቱ ውስጥ ፓምፕና ሞተርን የሚገናኘው (capler) ሞደፊክ ተደርጎ ከፕላስቲክ ቁስ ተሰርቶ በስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

ውሃ ከፓምፕ ገፍቶ ከወጣ በኋላ ወደኋላ እንዳይመለስ የሚያደርገው አካል (Non Return Valve) በዝገት ምክንያት በመበላሸቱ የተበላሸውን ብረት መልሶ ቅርጽ በማውጣትና በሌላ በመተካት የማስተካከል ስራ ተሰርቷል፡፡

በፓምፕ ውስጥ ውሃ በተገቢው እንዲዘዋወር የሚያደርገው የፕላስቲክ ቀለበት(ጋስኬት) በሰበቃ ምክንያት በማለቁ በሌላ የመተካት ስራ ተሰርቷል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

two × 1 =