ጣቢያው አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ እያሳለጠ ይገኛል

የይርጋለም2 ባለ 400/230/132/15 ኪ.ቮ. ማከፋፈያ ጣቢያ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የማከፋፈያ ጣቢያው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ኢርባ ገለጹ፡፡
አቶ ተስፋዬ እንደገለጹት በ2011 ዓ.ም. በይፋ ስራ የጀመረው ጣቢያው አራት ባለ 400 ኪ.ቮ ገቢ መስመር ፣ጥንድ ባለ 230 ኪ.ቮ.፣ሁለት ባለ 132 ኪ.ቮ. እና 3 ባለ 15 ኪ.ቮ. ወጪ መስመሮች አሉት፡፡
አራቱ ባለ 400ኪ.ቮ. ገቢ መስመሮች ሁለት ከወላይታ ሶዶ 2 እና ሁለት ከገናሌ ዳዋ 3 ኃ/ማ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ተስፋዬ ለይርጋለም ቁጥር1 እና ለዲላ ማከፋፈያ ጣቢዎች በ132ኪ.ቮ. ወጪ መስመር ኃይል ይሰጣል፡፡
ሶስቱን ባለ 15 ኪ.ቮ ወጪዎች ደግሞ ለአሉቶ ወንዶ እና ለጩኮ ከተሞች እና ለይርጋለም የተቀነባበረ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኃይል እየሰጠ እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል ፡፡
ከአዲስ አበባ በ320 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በሲዳማ ክልል ሲዳማ ክልል በይርጋለም ከተማ የሚገኘው የይርጋለም2 ባለ 400/230/132/15 ኪ.ቮ. ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ እየሠጠ ይገኛል፡፡
0 Comments