ጣቢያው አገልግሎቱን በብቃት፣ በጥራትና በተገቢው መንገድ እየሠጠ ነው

ከአዲስ አበባ በ319 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ክልል በሀላባ ከተማ የሚገኘው የሀላባ ባለ 230/132/15 ኪ.ቮ. ከፍተኛ ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎቱን በብቃት፣ በጥራትና በተገቢው መንገድ ኃይል እየሠጠ ይገኛል፡፡
የጣቢያው ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም ገበየው እንደገለፁት በ1982 ዓ.ም. ከሶዶ1 በ132 ኪ.ቮ. መስመር ኃይል በመቀበል ለሀላባ እና ለአካባቢው በ15 ኪ.ቮ. ኃይል በመስጠት በይፋ ሥራ የጀመረው ማከፋፈያ ጣቢያው እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ይሁንና በ2007 ዓ.ም. ማከፋፈያ ጣቢያው በተደረገለት የአቅም ማሣደግ ሥራ ኃይል የመቀበል አቅሙን ወደ 230 ኪ.ቮ ለማድረስ መቻሉን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ከአቅም ማሳደግ ሥራው በኋላ ማከፋፈያ ጣቢያው ሁለት ባለ 132 ኪ ቮ. እና አራት ባለ 15 ኪ.ቮ መስመሮች እንዲኖረው መደረጉን አንስተዋል፡፡በዚህም ተጨማሪ የኃይል አቅርቦት ጥያቄን ለመመለስ የሚያስችል አቅም እንደፈጠረለት ተናግረዋል፡፡
ከሆሳዕና በ230 ኪ ቮ. እና ከወላይታ ሶዶ በ132 ኪ.ቮ መስመር የሚቀበለውን ኃይል ባሉት አራት ባለ 15 ኪ.ቮ. ወጪ መስመሮች ሀላበ ከተማ እና ዱራሜ ወረዳ ጨምሮ በአካበቢው ለሚገኙ አካባቢዎች እና በ132 ኪ ቮ. ለሻሸመኔ ማከፈፈያ ጣቢያ ኃይል እየሰጠ ይገኛል፡፡
0 Comments