ጣቢያው በበጀት ዓመቱ 3248 ጊጋዋት ሰዓት ለማመንጨት አቅዷል

Published by corporate communication on

የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በበጀት ዓመቱ 3248 ጊጋዋት ሰዓት ለማመንጨት ማቀዱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢምረው ዳኜ ገለፁ፡፡

ሥራ አስኪያጁ እንደገለፁት የጣቢያው አራቱም ዩኒቶች በጥሩ ሁኔታ ላይ ስለሚገኙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተከናወነው የሚልቅ ኃይል ለማምረት ታቅዷል፡፡

የጥገና ባለሙያዎች አቅም እያደገ መምጣቱና ከሀገር ውጪም ሆነ ከማዕከል የጥገና ባለሙያ እስኪመጣ ሳይጠበቅ የሚሰራ ባለሙያ መፈጠሩ፣ ዩኒቶች በጥገና ምክንያት ከሥራ ውጪ የሚሆኑበት ጊዜ መቀነሱና የተሻለ የውሃ መጠን በክረምቱ እንደሚኖር ታሳቢ መደረጉ እቅዱን ከፍ አድርጎ ለማቀድ መነሻ ሆኗል ብለዋል፡፡

ጣቢያው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2773 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ በማምረት የዕቅዱን 90 በመቶ ያሳካ ሲሆን በዓመቱ ከተመረተው ኢነርጂ ውስጥ የ17 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻ ነበረው፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

sixteen + fifteen =