ጣቢያው ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት የሚያስችለው ተግባር አከናውኗል

Published by corporate communication on

የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በአካባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች ውሃና መብራት በማቅረብ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን የጣቢያው ኃላፊ አቶ ቢምረው ዳኜ ገለፁ፡፡

ኃላፊው እንደገለፁት በኃይል ማመንጫው አጠገብ ሆነው ቀደም ሲል ምንም ዓይነት መብራት የማያገኙት አህያ ጫንቃ፣ ገበሬ ማህበርና አውትሌት የተባሉት ቀበሌዎች ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

የኃይል መቆራረጥ የሚያጋጥማቸው ዳርፉር እና ቁንዝላ የሚባሉት ቀበሌዎች የኃይል አቅርቦታቸው እንዲሻሻል መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ለነዋሪዎቹ መስመር ሲዘረጋ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ግማሽ ወጪ መሸፈኑን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

ጣቢያው ሲጠቀምበት የነበረው የከርሰ ምድር ውሃ መጠኑ ቀንሶ ጣቢያ በቀን ለሁለት ሰዓታት ኃይል ጠዋትና ማታ ላይ ውሃ የሚያገኝ ቢሆንም ጉድጓዱን በማበልፀግ የአካባቢው ህብረተሰብም ውሃ እንዲያገኝ መደረጉን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡ 

እንደ አቶ ቢምረው ገለፃ መጠኑ ቀንሶ የነበረውን የውሃ ጉድጓድ ለማበልፀግ በአማራ የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ከ2 መቶ ሺህ ብር በላይ ተጠይቆ የነበረ ቢሆንም በጣቢያው ሠራተኞች ክህሎትና ጉልበት የውሃ መስመሩንና ፓምፑን የማደስ ሥራ ተሰርቷል፡፡

በቀጣይም በጣቢያው ያለውን የውሃ ችግር ለዘለቄታው ለመፍታት ተጨማሪ የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር ጥናት ተጠናቆ ተጓዳኝ ስራዎች ተጀምረዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

sixteen − ten =