ዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የኮሮና መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

Published by corporate communication on

ዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ሠራተኞች የሚውል ግምታቸው ከ430 ሽህ ብር በላይ የሆኑ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ ሳኒታይዘር እና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ እንደገለፁት ዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ ከግድቡ ግንባታ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ፕሮጀክቱ ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች የኤች አይ ቪ ኤድስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት የፋይናንስ፣ የቴክኒክና የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡

ዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ ከኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ሥራዎች በተጨማሪ ወቅታዊ ለሆነው የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉ በወረርሽኙ ምክንያት የፕሮጀክቱ ሥራ ተፅዕኖ እንዳይገጥመው አስጸዋፅኦ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

“ወደ ፊትም አብረን ሰርተን ግድቡን እውን እናደርጋለን” ብለዋል፡፡

የ ዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ ተወካይ ወ/ሮ የኔነሽ ታረቀኝ በበኩላቸው ድርጅቱ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ራሳቸውን ከኤች አይ ቪ- ኤድስ እንዲጠብቁ ሰፊ ሥራ መሰራቱን አስታውሰዋል፡፡

ቀደም ሲል አብሮ ለመስራት የተጀመረውን ስምምነት በማደስና በማጠናከር በቀጣይም አብሮ ለመሥራት መታሰቡንም ገልፀዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

10 − seven =