ዩኒቨርሲቲው ሲጠቀምበት የነበረውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስልጠና ማዕከል

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ ሲጠቀምበት የነበረውን የስልጠና ማዕከል ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያስረክብ ውሳኔ መተላለፉን የንብረት አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ አበበ ጉዲሳ እንደገለጹት ንብረትነቱ በቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የሆነና በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞው ወረዳ 28 ቀበሌ 2 በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር ነ-196/96 ተመዝግቦ የሚገኘውን የስልጠና ማዕከል ከ1988 ዓ.ም ጀምር ይህ ውሳኔ እስከተላለፈበት ድረስ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ሲጠቀምበት ቆይቷል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ሲጠቀምበት የቆየው ይህ ማዕከል በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ውሳኔ መሰረት ተሰጥቶ የቆየ መሆኑን ያስታወሱት አቶ አበበ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ንብረቱ እንዲመለስለት ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ጥያቄ በማቅረብ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውይይት ሲያካሂድ መቆየቱን አብራርተዋል፡፡

ይሁን እንጅ ዩኒቨርሲቲው ማዕከሉ የተሰጠው በወቅቱ በነበረው ጠቅላይ ሚኒስትር ውሳኔ መሆኑ በመግለጽ ለማስረከብ ፈቃደኛ እንዳልነበረ ነው አቶ አበበ የገለጹት፡፡

የኢትዮጳያ ኤሌክትሪክ ኃይልም ጥያቄውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒሰቴር በኩል በማቅረብ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አስከ አሁን ሲጠቀምበት የነበረውን የስልጠና ማዕከል ለባለቤቱ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እስከ መስከረም 2012 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲያስረከብ የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ውሳኔውን ተቀብሎ በርክክብ መርሃ ግብር ላይ ግን ልዩነቶች መኖራቸውን የማዕከሉን የርክክብ መርሃ ግብር ለማስፈፀም ከሁለቱ ተቋማት የተቋቋመው ኮሚቴ ጳጉሜ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ካካሄደው ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ለመረዳት ተችሏል፡፡

እንደ አቶ አበበ ገለፃ ዩኒቨርሲቲው ሲጠቀምባቸው ከነበሩት 30 በላይ ህንፃዎች ውስጥ የአምስት ህንፃዎች ርክክብ ጳጉሜ 4 ቀን 2011 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን በቀሪዎች ላይ በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ ልዩነት በመኖሩ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በውሳኔው መሰረት ርክክብ ለመፈፀም በአሁኑ ሰዓት ትምህርት የጀመሩ ተማሪዎች በመኖራቸው ሁሉንም ለማስረከብ እንደሚቸገር በምክንያትነት እንደሚያነሳ  አቶ አበበ ገልፀዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲውን ችግር በመረዳት የኢትዮጵያ ኤለሌክትሪክ ኃይል ሙሉ ህንፃዎችን እስከ 2012 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ርክክቡ እንዲፈፀም መርሃ

ርክክብ የተካሄደባቸው ህንፃዎችን ለተቋሙ ማሰልጠኛ ማዕከል እና ለቢሮ አገልግሎት ለማዋል መታሰቡን የጠቆሙት አቶ አበበ በአሁኑ ሰዓትም የጥገናና እድሳት ስራ እየተከናወነላቸው ነው ብለዋል፡፡

በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ የተቋሙ ንብረት የሆኑና መሰል ችግሮች ካሉ ንብረቶችን ለማስመለስ እየተሰራ ስላለው ስራ በተመለከተ ከዝግጅት ክፍላችን የተጠየቁት አቶ አበበ እስከ አሁን ድረስ የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩንና ይህ ነገር የሚታወቀው አብዛኛዎቹ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ስለሌላቸው የይዞታ ማረጋገጫ ሲወጣ ነው በማለት ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

16 − 5 =