የፐሮጀክቱ አፈጻጸም 97 ነጥብ 9 በመቶ ተጠናቋል

Published by corporate communication on

የኢዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሲዳማ ክልል እያስገነባ የሚገኘው የይርጋለም2 – ሀዋሳ2 ከፍተኛ የባለ 230 ኪ.ቮ. የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ግንባታ  97 ነጥብ 9  መጠናቀቁን የፕሮጀክቲ ሳይት ኃላፊ ገለጹ፡፡

ኃላፊው  አቶ ቴዎድሮስ  ጋሻው እንደገለጹት ፕሮጀክቱ ከይረጋለም2  400/230 ኪ.ቮ. ማከፋፈያ  አንስቶ  እስከ ሀዋሳ2 230/132 ኪ.ቮ. ድረስ የሚዘረጋ ጥንድ ባለ 230 ኪ.ቮ. መስመር ዝርታ ነው፡፡

የመስመር ዝርጋታውን ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ  47 ነጥብ 5 ኪ.ሜ  ርዝመት  የሚሸፍን የሽቦ ዝርጋታ   እና 116  ባለ 230 ኪ.ቮ. መሸከም የሚችል ታወር ማቆም ስራ ያካትታል፡፡

በአሁኑ ወቅትም 116 ታወሮችን የማቆምና የ42 ነጥብ 2 ኪ.ሜ. የሽቦ ዝርጋታ ተከናወኗል፡፡

በዚህም የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 90 ነጥብ 9 በመቶ መድረሱን  አስረድተዋል ፡፡

ቀሪውን 5ነጥብ 3 ኪ.ሜ .የሽቦ ዝርጋታ ለማጠናቀቅ ከካሳ ክፍያ ጋር  የተያያዙ ችግሮች እንቅፋት እንደሆነባቸው የገለጹት  አቶ ቴዎድሮስ  ችግሩን ለመፍታት ኮሚቴ ተዋቅሮ  በሚመለከታቸው አካላት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጨምረው አስገንዝበዋል፡፡

ችግሩ እንደተፈታ ባሉት ጥቂጥ ግዚያት  ስራውን ሙሉ ለሙሉ  ጨርሰው ለአገልግሎት ለማብቃት ዝግጁ ሆነው እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ኃላፊው ጠቁሟል፡፡

ስራውን ጨርሶ ለአገልግሎት ለማብቃት ከ56 ሚሎዮን ብር ባለይ የፋይናስ ወጪ የተመደበለት ሲሆን የሚሸፈነውም በኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡

ስራውን የኮንትራት ውል ወስዶ እየገነባ የሚገኘው በኢዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል  የሰብስቴሽን ትራንስሚሽን ኮንስተራክሽን ቢሮ የራስ አቅም የስራ ክፍል ነው፡፡

የመስመሩ መገንባት የትራንስሚሽን ኔትወርክ  ቀለበት ሲስተምን ለማጠናከር እና ተጨማሪ ኃይል ለማቅረብ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡     

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

5 × two =