የፈረንሳዩ አምባሳደር እና ልዑካቸው የቢሾፍቱ 3 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን ጎበኙ

Published by corporate communication on

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሚስተር ሬሚ ማሬሾ እና የልዑካን ቡድናቸው የቢሾፍቱ 3 ባለ 400/230/15 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን ጎብኝተዋል፡፡

አምባሳደር ሬሚ ማሬሾን፤ የፈረንሳይ ልማት ባንክ (AFD) ምክትል ዳይሬክተር እንዲሁም በአፍሪካ የኢትዮጵያ ተወካይን ያካተተው ልዑኩ ትናንት መስከረም 7 ቀን 2014 ዓ.ም ጣቢያውን ጎብኝተዋል፡፡

የጉብኝታቸው ዐቢይ ትኩረትም ከፈረንሳይ መንግስት በተገኘ ብድር የተገነባው የማከፋፈያ ጣቢያ ለህብረተሰቡና በአካባቢው ላሉ ኢንዱስትሪዎች የሚሰጠውን ፋይዳ ለማረጋገጥ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስሚሽንና አብስቴሽን ፕሮግራም ቢሮ II እና የትራ/ሰብ/ፕሮጀክት አስተዳደር I የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ገ/እግዝአብሔር የማከፋፈያ ጣቢያው ለአካባቢው ማህበረሰብና እና በዙሪያው ለተገነቡ ኢንዱስትሪዎች እየሰጠ ያለውን ፋይዳ አስመልክተው ለልዑኩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አምባሳደሩና የልዑካን ቡድናቸው በጉብኝቱ ወቅት በተሰጠው ማብራሪያ መደሰታቸውንና ማከፋፈያ ጣቢያው የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎትም አድንቀዋል፡፡

በቀጣይም የፈረንሳይ ልማት ባንክ (AFD) እንደዚህ ላሉ ፕሮጀክቶች ፈንድ በማመቻቸት ተቋሙን እና ሀገሪቱን ይረዳል ብለዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ከማከፋፈያ ጣቢያው በቀጥታ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙ የብረታብረት ማምረቻ ኢንዱስሪዎችንም ጎብኝቷል፡፡ 

53 ነጥብ 7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በሆነ ወጭ የተገነቡት የቢሾፍቱ ባለ 400/230/15፣ የዱከም እና ሞጆ ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች 85 ፐርሰንት ወጭ የተሸፈነው ከፈረንሳይ መንግስት በተገኘ ብድር መሆኑ ይታወሳል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

five × 1 =