የጨረታ ማስታወቂያ

Published by corporate communication on

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር EEP/PP/NCB/03/2015

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ በሚያስገነባው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምክንያት ለሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ውሃ የሚተኛበትን በስድስት (6) ሎቶች በመክፈል በቦታዎች ውስጥ ያሉትን ዛፎች ለመመንጠር፣ ጥቅም ላይ የማይውሉትን ለመከትከትና ለማቃጠል በማስፈለጉ ፍላጎት ያላቸውና መስፈርቱን የሚያሟሉትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች  በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
  2. አስር ሺ ሄክታር ደን ለመመንጠር በቂ ግብአቶች እና የሰው ሀይል ማቅረብ የሚችሉ እና ስራውን ለመስራት የስራ እቅድ እና የአሰራር ዘዴን በዝርዝር የሚያቀርቡና ለግብአቶቹ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  3. በቂ የመንቀሳቀሻ ካፒታል ያለባቸው
  4. ለሚከፈለው ቅድመ ክፍያ እና ለመልካም ስራ አፈፃፀም የባንክ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ
  5. ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ፕሮፖዛሎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/PP/NCB/03/2015 የሚል ምልክት በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የቴክኒካል ምዘናውን የሚያልፉ ተጫራቾች ብቻ ፋይናንሻል ፕሮፖዛላቸው የከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እና ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋናው መ/ቤት ኘሮኪዩርመንት ቢሮ የማይመለስ ብር 00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 800000 (ስምንት መቶ ሽህ ብር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡
  9. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 580781/0627 መደወል ይችላሉ ፡፡

 

 


0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

one × 5 =