የጊንጪ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ

ላርሰን ኤንድ ቱርቦ በተባለ የህንድ ኩባንያ የተገነባው የጊንጪ ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ፡፡
የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ገ/እግዝአብሔር እንዳስታወቁት የማከፋፈያ ጣቢያው መጠናቀቅ በጊንጭና በዙሪያው የሚገኙ ከተሞችን የኃይል መቆራረጥ ከማስቀረቱም በተጨማሪ ወደ ፊት አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል፡፡
የማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል የሚያገኘው ከገፈርሳ – ጌዲዮን ከተዘረጋው ባለ 230 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ሲሆን ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች ተተክለውለታል፡፡
ጣቢያው ሁለት ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ገቢ እና 10 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡
በ2008 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪው 67 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ነው፡፡
0 Comments