የጊቤ III የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ የውኃ መጠኑ ከፍታ ጨመረ

Published by corporate communication on

 የጊቤ III የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ውኃ የመያዝ አቅሙ 880.2 ሜትር ኪዩብ ከባህር ጠለል በላይ የደረሰ ሲሆን ከዓለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ19.2 ሜትር ከፍ ብሎ ይገኛል፡፡

የጊቤ III የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ሰሙ እደገለፁት ባለፈው ዓመት ግድቡ አጠቃላይ ይዞት የነበረው ውኃ 861 ሜትር ኪዩብ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

ግድቡ በሙሉ አቅሙ ኃይል ለመስጠት 892 ሜትር ኪዩብ ውኃ መያዝ ይኖርበታል የተባለ ሲሆን የዝናቡ ሁኔታ ባለበት የሚቆይ ከሆነ የውኃ መጠኑ በሙሉ አቅሙ ኃይል ወደ ሚሰጥበት ከፍታ ይደርሳል ብለዋል ሥራ አስኪያጁ፡፡

እስከ መስከረም አጋማሽ የግድቡ የውኃ ከፍታ በእየቀኑ በአማካይ 55 ሴንቲ ሜትር ጭማሪ እያሳየ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ሀብታሙ ወደ ፊት በአስተማማኝ ደረጃ ኃይል እንዲሰጥ ከተፈለገ ውኃ የመያዝ አቅሙ ላይ ትኩረት መደረግ አለበት ብለዋል፡፡

በዚህ ዓመት ያለው የውኃ ከፍታ ከግንባታው ወዲህ የመጀመሪያው ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ይህም የግድቡ ኃይል የማመንጨት አቅም አስተማማኝ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን አመላካች ነው ተብሏል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

17 + nineteen =