የውሃ ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ አካሔደ

የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በስሩ ከሚገኙ ተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ጫንጮ ደርባን ሲሚንቶ ፋብሪካ አካባቢ ተገኝተው የችግኝ ተከላ አከናውነዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ፍሬህይወት ወልደሃና የአሁኑን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ለየት የሚያደርገው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት ባጠናቀቅንበት ማግስት የተካሄደ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉትን ችግኞችን በመንከባከብ ከዳር ማድረስ ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ ልማት በቀጣይ የብልፅግና ዓመታትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
የችግኝ ተከላ ከማከናወን ጎን ለጎን ሁሉም ዜጋ ራሱን እና ማህበረሰቡን ከኮሮና ቫይረስ መጠበቅ እንዳለበትም ዶክተር ፍሬህይዎት አሳስበዋል፡፡
የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዲኤታ ዶክተር ፍሬህይዎት ወልደሃና፣ ዶክተር ካባ ኡርጌሳን ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና ሠራተኞች በዚህ መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተዋል፡፡
0 Comments