የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የ2012 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገሙ

Published by corporate communication on

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2013 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ተወያዩ፡፡

በውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተካሄደው የአፈፃፀም ግምገማና የዕቅድ ውይይት ላይ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በተጨማሪ የውሃ ልማት ኮሚሽን፣ የውሃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት፣ የመስኖ ልማት ኮሚሽን፣ የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን፣ የብሔራዊ ሜትርዎሎጂ ኤጄንሲ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን እና የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት መሥሪያ ቤቶች እቅድ አፈጻጸምና የ2013 በጀት ዓመት እቅዶች ቀርበው ግምገማና ውይይት ተካሂዷል፡፡

የግምገማና ውይይት መድረኩን የመሩት የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ባለፈው በጀት ዓመት በዘርፉ የተከናወኑ ሥራዎችን በዝርዝር ከገለጹ በኋላ ከሕዝቡ ፍላጎት አንጻር በቀጣዩ ጊዜ ተግቶ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የታላቁ ሕዳሴ ግድብን በሚመለከት በቀጣይ ዓመት ኃይል ማመንጨት እንደሚጀመር፣ የአስራ አንድ ተርባይኖች ተከላ እንደሚከናወንና ሁለተኛው ዓመት የውሃ ሙሊት ለማከናወን ሥራዎች እንደሚሠሩ ጠቁመዋል፡፡

ከህዳሴው ግድብ ግንባታ ጎን ለጎንም ወደፊት ግድቡ ሲጠናቀቅ በልዩ ልዩ ዘርፎች ሊሠሩ ስለሚገባቸውም ጉዳዮች በመንግሥት ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ እንደሆነ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በውይይቱ ላይ የየዘርፉ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የየተቋማቱ ምክትል ኃላፊዎችና መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

ነሐሴ 6 ቀን 2012 ዓ.ም

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

14 − four =