የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ግንባታ 35 በመቶ ደረሰ

Published by corporate communication on

የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ግንባታ 35 ነጥብ አንድ በመቶ መድረሱን የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ የኮይሻን ግድብ ግንባታ በተመለከተ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ እስከ ነሐሴ 2012 ዓ.ም ድረስ አፈጻጸሙ 35 ነጥብ አንድ በመቶ ደርሷል።

ሁለት ሺህ 160 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ በሚፈለገው የግንባታ ፍጥነት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የግድቡን ግንባታ በአምስት ዓመት ተኩል ለማጠናቀቅ ውል የተገባ መሆኑን አማካሪው አስታውሰው በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ በመንግስት በኩልም አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የኮይሻ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የሲቪል ስራውን ሳሊኒ በስራ ተቋራጭነት እየገነባው ይገኛል፡፡

እንደ አቶ ሞቱማ ገለፃ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት 92 በመቶ የሚሆነው ከውሃ የሚገኝ ሲሆን ይህንን ድርሻ ወደ 70 በመቶ ዝቅ ለማድረግ ከተለያዩ ታዳሽ የኃይል ምንጮች ለማሰባጠር እየተሰራ ይገኛል፡፡

መንግስት የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ለማስፋትና ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉትን ኃይል ለማሟላት የኮይሻን የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫና የታላቁን የህዳሴ ግድብ ጨምሮ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

3 × 4 =