የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ እውነታዎች
Published by biniyam melese on
- ፕሮጀክቱ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኮንታ ልዩ ወረዳ እና በጎፋ ዞን መለኮዛ ወረዳ መካከል ይገኛል::
- ከአዲስ አበባ በጅማ መስመር 540 ኪ.ሜ እንዲሁም በወላይታ ሶዶ መስመር 560 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል::
- ግድቡ ከጊቤ III የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በ129 ኪ.ሜ ያህል ይርቃል::
- የግድቡን ግንባታ ለማስጀመር የኮንትራት ሥምምነት የተካሔደው መጋቢት 19 ቀን 2008 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ በመጋቢት 28 ቀን 2016) ነው::
- የግድቡ አይነት- የአርማታ ሙሌት (Roller Compact Concrete)
- የግድቡ ቁመት – 170 ሜትር
- የግድቡ ርዝመት ወደ ጎን – 990 ሜትር
- የግድቡ ውሃ የመያዝ አቅም – 6,500 ሚሊዬን ሜትር ኪዩብ
- የተፋሰሱ ስፋት – 44,325 ካሬ ኪ.ሜ
- ግድቡ የሚፈጥረው ሃይቅ ስፋት – 100 ካሬ ኪ.ሜ
- የማመንጨት አቅም- 2,160 ሜጋዋት
- ዓመታዊ የኃይል ምርት አቅም – 6,460 ጊጋ ዋት በሰዓት
- 8 ተርባይኖች የሚገጠሙለት ይሆናል::
- 3 የውሃ ማስገቢያ (Penstock) ቱቦዎች ይኖሩታል::
- 20 ሜትር ስፋት እና 17 ሜትር ቁመት ያለው ባለ 6 የውሃ ማስተንፈሻ (Spillway) ቱቦዎች አሉት::
- የግድቡን ግንባታ የሚያከናውነው የጣሊያኑ ሳሊኒ ኢምፕሪጅሎ ኤስ.ፒ.ኤ (Salini Impregilo SPA) ኩባንያ
- የፕሮጀክቱ አማካሪ የቤልጀሙ ትራክቴብል ኢንጅነሪንግ (Tractebel – Engie)
- አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ወጪ – 2.5 ቢሊዬን ዩሮ
0 Comments