የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ክለብ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነ

Published by corporate communication on

የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ክለብ በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን አዘጋጅነት በተካሔደው

ሻምፒዮና ሶስተኛ በመውጣት የነሃስ ሚዳሊያ እና የሰባት ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በተካሔደው የማጣሪያ ውድድር ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ መጨረሻው የዋንጫ ፉክክር

የገባው የኤሌክትሪክ ክለብ ከስድስት ክለቦች ጋር እጅግ ፈታኝ ፉክክር በማድረግ ከአምስት ጨዋታዎች ስምንት ነጥብ

ሰብስቦ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፡፡

በዚህ ውድድር ተጋባዥ የሆነው የአዳማ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ክለብ የዋንጫ ባለቤት ሲሆን የመድን እግር ኳስ ክለብ ደግሞ የብር ሜዳሊያ አግኝቷል፡፡

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን  ኮሚሽነር አስራት ኃይሌ ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባ እግር ኳስን በማሳደግ እና ተሳታፊዎችን በማብዛት በስፖርቱ ዘርፍ ለሀገር የሚጠቅሙ ተተኪ ወጣቶችን ማፍራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት በሚደረገው ጥረትም በከተማዋ የሚገኙ ባለሀብቶች በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ

እንዲያደርጉ ኮሚሽነር አስራት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን የ2013 ዓ.ም የእግር ኳስ ውድድሮች መጠናቀቃቸውን አስመልክቶ በትናንትናው ዕለት የመዝጊያ መርሀ ግብር በአበበ ቢቄላ ስቴዲየም ያዘጋጀ ሲሆን በዕለቱም ታዋቂ የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ ለአሸናፊ ክለቦች የዋንጫ እና የሜዳሊያ ሽልማት የተሰጠ ሲሆን ለምስጉን ዳኞች፣ ለኮከብ ተጫዋቾች እና ኮከብ አሰልጣኞች የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት መርሀ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

16 − 2 =