የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኦፕሬሽን ስራዎቹን ለማሻሻል የሚያስችሉ እርምጃዎች እየወሰደ ነው

Published by corporate communication Editor on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኦፕሬሽን ስራዎቹን ለማሻሻል የሚያስችሉ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ዶ/ር አብርሃም በላይ ገለፁ።

የአዳማ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫን የጎበኙት ዋና ስራ አስፋፃሚው ከጣቢያው ሰራተኞችና ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

ሰራተኞቹ የክህሎት ክፍተታቸውን የሚሞላ ስልጠና እንዲመቻችላቸው፣ ከደመወዝ፣ ከመሰረተ ልማት፣ ከቤት እና ከአበል ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንዲስተካከሉላቸው ጠይቀዋል።

ከግዢ ጋር የተያያዙ መዘግየቶች የአመራሩን ትኩረት የሚሹ መሆናቸውን አንስተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው በበኩላቸው ሰራተኞቹ ያነሱትን ጥያቄ ለመመለስና ጥቅማ ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር የሚያስችሉ ማሻሻያዎች ለማከናወን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

እንደ ጥያቄዎቹ ባህርይ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የሚፈቱ ጉዳዮችን በመለየት ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

እንደ ስራ አስፈፃሚው ገለፃ ለኦፕሬሽን ስራዎች የተሰጠው ትኩረት ሰራተኛውን በቦታው እንዲቆይ የሚያደርግና አዳዲስ ሰራተኞችን ለመሳብ ያስችላል።

የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ስራዎች ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዳርጌ እሸቴ በበኩላቸው የዘርፉን አፈፃፀም ለማሻሻል ሁሉም በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።

የዋና ስራ አስፈፃሚው ጉብኝት የሰራተኛውን የስራ ተነሳሽነት የሚጨምር በመሆኑ እንዲቀጥል ሰራተኞቹ ጠይቀዋል።

Categories: ዜና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

20 − 9 =

Facebook