የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ሠራተኞች ደም ለገሱ

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ሠራተኞች “ደም እንለግስ፤ ህይወት እንታደግ” በሚል መሪ ቃል ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም የደም እጥረት ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሚውል ደም ለግሰዋል፡፡

ተቋሙ የኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ኃይል ከማመንጨት ሀገራዊ ተልዕኮው ባለፈ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል፡፡

በዛሬው ዕለትም በተለያዩ ምክንያቶች ደም ለሚያስፈልጋቸውና በደም ዕጦት ምክንያት ህይወታቸው አደጋ ላይ የወደቀ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመታደግ የተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች ደም በመለገስ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡

የተደረገው የደም ልገሳ በጤና ተቋማት የሚያጋጥመውን የደም እጥረት ለመቅረፍ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡

ደም ሲለግሱ ያገኘናቸው የተቋሙ ሠራተኞች ደም መለገስ በመቻላቸው እንደተደሰቱ እና በቀጣይ መሰል ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የደም ልገሳ መርሀ ግብሩ ለሀገር የሚከፈል ዋጋን መደገፍ ነው ያሉት ሠራተኞቹ የሚለገሰው ደም ለአንድ የቤተሰብ አባል እንደሚውል በማሰብ ሁሉም ሊሳተፍበት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት የተንቀሳቃሽ ደም ለጋሾች ባለሙያ ሲስተር ዘውዴ ግዛቸው እንደገለጹት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ሠራተኞች በደም እጥረት ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ የበርካታ ወገኖቻቸውን ህይወት መታደግ እንደሚቻል በመረዳት በዚህ በጎ ተግባር ላይ በመሳተፋቸው ሊመሰገኑ ይገባል፡፡

ሌሎች ተቋማትም ይህን አርዓያ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

20 + 19 =