የኢትዮያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮንትራት ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገቢን ለማሳደግና ወጪን ለመቀነስ የሚያስችል የማማከር ስራ ለማከናወን ኤ ኤፍ ሜርካዶስ እና ኤ ኤፍ ኮንሰልት (AF-Mercados and AF Counsult) ከተሰኙ የስፔን ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡
የፊርማ ስነ ስርዓቱን የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢንጅነር አብርሃም በላይ እና የኤ ኤፍ ሜርካዶስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ሚጉኤል ሄርናንዴዝ (Miguel A. Hernandez) ተፈራርመዋል፡፡
ዶ/ር አብርሃም በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደተናገሩት ተቋሙ ገቢውን ለማሳደግ የተለያዩ አማራጮችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን ይህ ስምምነት የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ እና ወጪውን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ ተቋሙ ለኩባንያዎች አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡
የኤኤፍ ሜርካዶስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ሚጉኤል ሄርናንዴዝ በበኩላቸው ኩባንያቸው ከዚህ በፊት በምስራቅ አፍሪካ በኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክቶች ላይ በማማከርና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የበርካታ አመታት ልምድ እንዳለው ገልዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም ኩባንያቸው በኤሌክትሪክ ዘርፍ ላይ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መሳተፉን ጠቁመው በቀጣይ ከተቋሙ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳለቸው አስታውቀዋል፡፡
በተቋሙ የግዥ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ከፍያለው መርጊያ እንደተናገሩት ስምምነቱ የተካሄደው ከገቢ ማሰዳግና ወጪ ቅነሳ ጋር በተያያዘ የእያንዳንዱ የስራ ዘርፍ ያለበትን የአሰራር ሁኔታ ጥናት ለማጥናት፣ ጥናቱን መሰረት በማድርግ ገቢን እንዴት ማሳደግ እመንደሚቻልና እንዴት ወጪን መቀነስ እነደሚገባ አዲስ የአሰራር ስርዓት ለማጥናት፣ ወደፊት ተቋሙ የሚመራባቸው የተለያዩ የአሰራር ማንዋሎችንና ፖሊስዎችን ለማዘጋጀት እና ስልጠና ለመስጠት ነው ብለዋል፡፡ ይህን ስራ ሁለቱ ኩባንያዎች በጥምረት እንደሚያከናውኑትም ታውቋል፡፡
የማማከር ስራዉን ለማከናወን ለአንድ አመት የሚቆይ ስምምነት መደረጉን የጠቆሙት አቶ ከፍያለው ስምምነቱ ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር የሚሸፈን የ68 ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
እንዴ አቶ ከፍያለው ገለፃ ተቋሙ ከዚህ በፊት የነበረው የወጪና ገቢ ሪፖርት ስርዓት ምን እንደሚመስል ለግብዓትንት የሚያገለግሉ መረጃዎችን በመስጠት በኩል ለኩባንያዎች ድጋፍ ያደረጋል ብለዋል፡፡
0 Comments