የአይኤስኦ የጥራት ሥራ አመራር (ISO Quality Management) ሥልጠና እየተሰጠ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን የአይኤስኦ የጥራት ሥራ አመራር (ISO Quality Management) ሥልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡
ሥልጠናው ሥራ አመራሩ ከጥራት ማኔጅመንት ጽንሰሐሳብ ጋር እንዲተዋወቅ፤ ዓለምአቀፍ አሰራሮችን እንዲረዳና የኦፕሬሽን ቅልጥፍና እንዲያመጣ እንዲሁም የደንበኞችን እርካታ እንዲያሳድግና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲያመጣ ያግዛል ተብሏል፡፡
በስልጠናው ላይ የአይኤስኦ የጥራት ሥራ አመራር ጽንሰሐሳብ፣ መርሆዎችና ጥቅም፣ ሂደትና ስጋት ሥራ አመራር ላይ ትኩረት ያደረጉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡
ሥልጠናውን በመስጠት ላይ የሚገኘው በዓለም አቀፍ ደረጃ የኦዲት፣ የታክስና የማማከር አገልግሎት የሚሰጠው KPMG ዓለምአቀፍ ነው፡፡
0 Comments