የአዋሽ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

Published by corporate communication on

በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በጎርፍ ተጥለቅልቆ አገልግሎት አቋርጦ የነበረው የአዋሽ 3  የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ላለፉት 49 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውና 32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአዋሽ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት ከነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቁሞ ነበር፡፡

በወቅቱ ከተርባይን ወለል እስከ ተርባይን ሮተር ማገናኛ ዘንግ (Turbine Rotor Coupling Shaft) ድረስ ያሉት የኤሌክትሮ-መካኒካል እቃዎች በውሃ ተውጠው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

ለሁለት ወራት አካባቢ አገልግሎት አቋርጦ የነበረው ጣቢያ አንድ ዩኒት ወደስራ ማስገባት በመቻሉ ጣቢያው በከፊል ስራ የጀመረ ሲሆን ቀሪውን አንድ ዩኒት ስራ ለማስጀመር በሂደት ላይ ይገኛል።

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

eight − two =