የአሉቶ ጂኦተርማል የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሚያዝያ 10 የጉድጓድ ቁፋሮው ይጀመራል

የአሉቶ ላንጋኖ ጂኦተርማል የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሚያዝያ 10 ቀን 2013 ዓ/ም የጉድጓድ ቁፋሮ እንዲጀመር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ አቅጣጫ አስቀመጡ።
ለሥራው መጀመር የውሃ አቅርቦት ወሳኝ በመሆኑ ቀሪ ስራዎቹ በፍጥነት እንዲጠናቀቅም ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ንጉሴና ፕሮጀክቱን በፋይናንስ የሚደግፈው የዓለም ባንክ ተወካዮች እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን በስፍራው በመገኘት ገምግመዋል።
የአሉቶ ላንጋኖ የከርሰ ምድር እንፋሎት 7 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ 70 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ይኖረዋል።
0 Comments