የአሉቶ ጂኦተርማል የማስፋፊያ ፕሮጀክት የእንፋሎት ፍለጋ ቁፋሮው 138 ሜትር ደርሷል

Published by corporate communication on

ግንቦት 21 ቀን 2013 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው የአሉቶ ላንጋኖ የከርሰ ምድር እንፋሎት የማስፋፊያ ፕሮጀክት የእንፋሎት ፍለጋ የጉድጓድ ቁፋሮ 138 ሜትር መድረሱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአሉቶ ጂኦተርማል ፕሮጀክት አስታወቀ።

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ መሳይ ፈቃዱ እንደገለፁት ከደህንነት (safety) ጋር በተያያዘ ቁፋሮው ለሳምንታት እንዲቆም ተደርጎ ነበር፡፡

አሁን ላይ ከደህንነት ጋር የተያያዙ መስፈርቶች ስለተሟሉ ቁፋሮው ዛሬ እንዲቀጥል  ተደርጓል።

እንደ አቶ መሳይ ገለፃ የእንፋሎት ፍለጋ የጉድጓድ ቁፋሮው ወደ ከርሰ ምድር እስከ 2 ሺህ 700 ሜትር ጥልቀት የሚኖረው ሲሆን እስከ 70 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ታስቦ እየተሰራ ነው፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

fifteen − 7 =