የነገ ብርሃናችን በዛሬ ላባችን ተጽፏል

Published by corporate communication on

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ የኃይል ማመንጨት ሥራውን ዛሬ በይፋ ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ የመጀመሪያው ተርባይን በይፋ ኃይል ማምረቱን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ከአባይ ተፋሰስ ሀገራት ጋር በጋራ ለመጠቀም ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየችበት የትብብር ተምሳሌት ሆኗል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተሳተፈበት ታላቂ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተቋሙ ሠራተኞች፣ አመራሮችና የስራ አመራር ቦርድ እንዲሁም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያልተቋረጠ ድጋፍና አመራር እንዲሁም ቀጥተኛ ተሳትፎ ፕሮጀክቱ አሁን ላለበት ደረጃ እንዲደርስ አድርገውታል ብለዋል።

የግድቡ ግንባታ መሰረት ከተጣለ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች አሻራቸውን ማሳረፋቸውን ሥራ አስፈፃሚው በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።

እንደ ሥራ አስፈፃሚው ገለፃ ግድቡ በተገነባበት ቦታ ላይ በርካቶች መስዋዕትነት በመክፈል የነገ ብርሃናችንን በዛሬ ላባቸው ጽፈዋል።

ለዚህም በተቋሙና በራሳቸው ስም ምስጋናቸውን በማቅረብ ለሁሉም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

3 × 4 =