የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 76.35 በመቶ ደረሰ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 76 ነጥብ 35 በመቶ መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን፣ በመስኖ ልማት፣ በኢነርጂ እንዲሁም በተፋሰስና የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዙሪያ የ2013 የሩብ ዓመት የስራ ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በተያዘው 2013 ዓ.ም ሁለቱ ተርባይኖች ኃይል እንዲያመነጩ ለማስቻል በሩብ ዓመቱ የግንባታውን አፈፃፀም በ1 ነጥብ 6 በመቶ ለማሳደግ ታቅዶ በ2 ነጥብ 05 በመቶ ለማሳደግ መቻሉን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ገልፀዋል፡፡
በዚህም በሩብ ዓመቱ የግንባታውን አፈፃፀም ከታቀደው በላይ ለማከናወን መቻሉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በመስኖ ግድቦች ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ በመያዙ የተያዘውን ውሃ ወደ ልማት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ዶ/ር ስለሺ ገልፀዋል፡፡
በንፁህ መጠጥ ውሃ እና በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ዙሪያም በሩብ ዓመቱ አበረታች ሥራ መሰራቱን ሚንስትሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአየር ክልል ከበረራ ነፃ እንዲሆን የተደረገው ያለውን የደህንነት ስጋት ለማስቀረት ነው ብለዋል፡፡
በዕቅዱ መሰረት በተያዘው ዓመት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ኃይል እንዲያመነጩ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል፡፡
0 Comments