የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ተጠናቀቀ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ስራ በስኬት ተጠናቋል።
የሁለተኛው ዙር ውሃ ሙሌት በቅርቡ ኃይል የማመንጨት ስራ ይጀምራሉ ተብለው የሚጠበቁትን ሁለቱን ዩኒቶች ለማንቀሳቀስ በቂ ውሃ እንዲይዝ ያስችሏል።
ይህም ባለፈው ዓመት ከተያዘው የመጀመሪያው የውሃ መጠን ጋር ተደምሮ ሁለቱንም ዩኒቶች ዓመቱን ሙሉ ኃይል እንዲያመነጩ የሚያስችል ነው።
በአሁኑ ወቅትም ቀድመው ኃይል ለሚያመነጩት ዩኒት 9 እና 10 ኃይል ማመንጫዎች የተርባይንና ጀነኔተር ተከላ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
በዘንድሮ ክረምት ወቅትም ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ወደ ግድቡ ሲገባ የነበረ በመሆኑ ሙሊቱ ከታሰበው ጊዜ ቀድሞ እንዲጠናቀቅ አድርጎታል።
የመጀመሪያው ዓመት የውሃ ሙሊት ልክ በዛሬው ዕለት እንደተከናወነ ይታወሳል።
0 Comments