የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራዎችን በአዲስ ኃይል ወደቀድሞ ፍጥነት ለመመለስ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

Published by corporate communication Editor on

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራዎችን በአዲስ ኃይል ወደቀድሞ ፍጥነት ለመመለስ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ በዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም በላይ የተመራ የልዑካን ቡድን የግድቡን የሲቪልና የብረታብረት ስራዎች ጎብኝቷል፡፡ የግንባታው አማካሪዎች ትራክትቤል ኢንጂነሪንግና ኤልክ ኤሌክትሮ ኮንሰልት ተወካዮች እንደገለፁት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ለታዩት ችግሮች ቴክኒካዊ መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው። ቀደም ሲል የተጀመሩና የተከናወኑ ከብረታብረት ጋር የተያያዙ ስራዎች ከ90 በመቶ በላይ ፍተሻ ተደርጎ ችግሮቹን ለማረም የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውም ተገልጻል። የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደተናገሩት የግድቡ የግንባታ ስራዎች መነቃቃት እየታየባቸው ነው። በመሆኑም የተለያዩ ሂደቶችን ማለፍ የማይጠይቁ የግንባታ ስራዎች በፍጥነት እንዲከናወኑ ሚኒስትሩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም በላይ በበኩላቸው የግድቡ ግንባታ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት ለማረምና ጉድለቱን ለማካካስ ተቋማቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የግድቡን ግንባታ ለማፋጠን ቀደም ሲል ከብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር በንዑስ ተቋራጭነት ለመስራት ውል የነበራቸው ተቋራጮች መካከል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከጂ ኢ ኃይድሮ ፍራንስ ጋር ውል ተፈራርሟል፡፡

Categories: ዜና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

nine + four =

Facebook