የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በይፋ መጀመሩን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አበሰሩ

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በይፋ መጀመሩን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ እንደገለፁት የግድቡን ተፈጥሯዊ የግንባታ ሂደት በጠበቀ መልኩ ሙሌቱ እየተከናወነ ነው፡፡
ግድቡን በተመለከተ በሳተላይት ውሃ እየተሞላ መሆኑን የሚያሳዩት ምስሎች ትክክለኛ መሆናቸውንም ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡
በተለያዩ የመረጃ መረቦች ከተሰራጩት ምስሎች በተጨማሪ የአውሮፓ ስፔስ ኤጀንሲው ሴንቲኔል-1 ከቀናት በፊት የግድቡ የዉሀ ሙሌት መጀመሩን የተመለከተ የሳተላይት ምስል አውጥቷል፡፡
ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የምታደርገው ድርድር የአሁኑን ትውልድ ብቻ ሳይሆን የመጪውን ትውልድ ጥቅም በሚያስጠብቅ መልከ የሚደረግ ይሆናልም ብለዋል፡፡
0 Comments