የታላቁ ህዳሴ ግድብ የጀነሬተር አንቀሳቃሽ አካል( Rotor) የማስቀመጥ ሥራ ዛሬ በስኬት ተከናወነ

በቅርቡ ኃይል እንደሚያመነጭ ከሚጠበቁት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለት ዩኒቶች መካከል በዩኒት 10 ላይ የተርባይን ጀነሬተር ተሽከርካሪ አካል (Rotor) በቦታው ላይ የማስቀመጥ ሥራ ዛሬ በስኬት ተከናውኗል።
ሮታሩና አብረው ያሉት አካላት 840 ቶን ክብደት ያላቸው ሲሆን ሮተሩ ብቻውን 780 ቶን ይመዝናል።
ሮተሩ ከአንድ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ድረስ ያለው አጋማሽ ርዝመት ወይም ዳያሜትር 11 ነጥብ 7 ሜትር ነው።
የሮተሩና የተርባይን አካላቶች በአግባቡ መገጠም የኃይል ማመንጨት የሙከራ ስራ ለመጀመር መቃረቡ አመላካች ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
0 Comments