የቱሉሞዬ ጂኦተርማል ፕሮጀክት የመጀመሪያው ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቋል

Published by corporate communication on

በአርሲ ዞን ኢተያ አካባቢ የተጀመረው የቱሉሞዬ የከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይል ማመንጫ ግንባታ ፕሮጀክት 150 ሜጋዋት ኃይል ለማግኘት በሁለት ምዕራፎች እየተከናወነ ነው፡፡

የቱሉሞዬ ጂኦተርማል ኢነርጂ የቴክኒክ ኃላፊ ስጉርጉር ጌሪሰን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ የምትገኝ ሀገር በመሆኗ  የእንፋሎት ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ከፍተኛ እምቅ አቅም አላት፡፡

በቱሉሞዬም እስከ 2000 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚያስችል እምቅ የእንፋሎት ኃይል መኖሩን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በሁለት ምዕራፎች 150 ሜጋዋት ኃይል ለማግኘት 10 የተለያዩ ጉድጓዶች እንደሚቆፈር የገለፁት ኃላፊው ለሥራው የሚያግዙ ሦስት የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ መጠናቀቁንና አራተኛውም በጅምር ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ ሩፋት ማይና በበኩላቸው የመጀመሪያው የኃይል ማመንጫ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቆ ወደ ሁለተኛው ቁፋሮ መገባቱን ተናግረዋል፡፡

ወደ መሬት ውስጥ መቆፈር ከሚያስፈልገው 2500 ሜትር ውስጥ አሁን ላይ 1014 ሜትር መቆፈሩንም ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን ሲጠናቀቅ ደግሞ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ባሻገር የተለያዩ የሥራ አማራጮችን መፍጠር እንደሚያስችል ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በቱሉሞዬ ጂኦተርማል እና በኬንያው ኬንጄን ኩባንያዎች እየተከናወነ የሚገኘው የቱሉሞዬ የከርሰ ምድር እንፋሎት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ በ800 ሚሊዬን ዶላር ወጪ የሚከናወን ሲሆን የግንባታ ሥራውም ሁለት ዓመታትን ይፈጃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

5 − two =