የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ከግሪድ ጋር ማገናኘት ተችሏል

Published by corporate communication on

የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ከብሔራዊ የኃይል ቋት (ግሪድ) ጋር የማገናኘት ስራ በስኬት ተከናውኗል።

ጣቢያው ከብሔራዊ የኃይል ቋት (ግሪድ) ጋር የሚገናኝበት  መስመር በመቋረጡ  ምክንያት ለወራት ኃይል ማመንጨት አቁሞ እንደነበር ይታወሳል።

ከመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ግን በጊዜያዊነት  ከሲስተም ጋር ሳይገናኝ ራሱን በራሱ እየተቆጣጠረ  (Isolated mode) ኃይል ሲሰጥ ቆይቶ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከግሪድ ጋር እንዲገናኝ ተደርጓለ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመሆኒ መቀሌ ያለው መስመር ከተከዜ-  መቀሌ ከተዘረጋው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ኃይል እንዲያገኝ ማድረግ ተችሏል።

ቀደም ሲል ከአላማጣ መኾኒ አሸጎዳ መቀሌ የሚሄደው መስመር ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ ተቋርጦ እንደነበር መግለፃችን አይዘነጋም።

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

nine + ten =