የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ዛሬ ወደ ኃይል ማመንጨት ስራው ተመለሰ

Published by corporate communication on

ለወራት ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ የቆየው የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ  ዛሬ ሥራ ጀመረ።

የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ከብሔራዊ የኃይል ቋት (ግሪድ) ጋር የሚገናኝበት  መስመር በመቋረጡ  ምክንያት ኃይል ማመንጨት አቁሞ እንደነበር ይታወሳል።

ከተከዜ-  መቀሌ በተዘረጋው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ሲደረግ የነበረው ጥገና በመጠናቀቁ ዛሬ ቀን ከ 7:18 ሰዓት ጀምሮ በጊዜያዊነት  ከሲስተም ጋር ሳይገናኝ ራሱን በራሱ እየተቆጣጠረ  (Isolated mode) ኃይል መስጠት ጀምሯል።

በአሁኑ ሰዓት ጣቢያው ካሉት አራት ዩኒቶች መካከል በሁለት ዩኒቶች እስከ  108 ሜጋ ዋት ድረስ ኃይል እየሰጠ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ካለፈው ሐሙስ ከሰዓት ጀምሮ በትግራይ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ ከተከዜ ኃይል ማመንጫወደ መቀሌ የሚሄደው  መስመር ተጠግኖየተከዜ ኃይል ማመንጫ  ስራ በመጀመሩ ዳግም አገልግሎት ማግኘት ጀምሯል።

ቀደም ሲል ከአላማጣ መኾኒ አሸጎዳ መቀሌ የሚሄደው መስመር ላይ ባጋጠመችግር ምክንያት የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ ተቋርጦ ነበር።

በትግራይ በተካሄደውን የህግ ማስከበር ተከትሎ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የተከዜ ግድብ ደግሞ መንግስት በአውሮፕላን ደብድቦ አፍርሶታል ተብሎ የሀሰት ወሬ ተናፍሶ ነበር።

በወቅቱም በግድቡ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰ መግለፃችን ይታወሳል።

የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በአራት ዩኒቶች 300 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ባለ ጥምር ቅስት (double arc)ቅርፅ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ነው።

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

two + 2 =