የተቋሙ ጋራዥ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳኑን አሰታወቀ

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋራዥ ለድርጅቱ ተሸከርካሪዎች ቀላል፣ መካከለኛ እና ከባድ ጥገናዎች በመስጠት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳኑን የተሽከርካሪ ጥገና ከፍተኛ ኦፊሰር አቶ ብሩክ እንዳለ አስታወቁ፡፡

በበጀት ዓመቱ ጋራዡ የሰጠው  የጥገና አገልግሎት በውጪ ድርጅቶች  ቢከናወንላቸው ኖሮ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይደረግባቸው እንደነበር የጠቀሱት አቶ ብሩክ ጥገናው በተቋሙ ጋራዥ ከ6 ሚሊዮን ብር ባልበለጠ ዋጋ በመከናወኑ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ተችሏል ብለዋል፡፡

እንደ ከፍተኛ ኦፊሰሩ ገለፃ በበጀት ዓመቱ ለ801 የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች የቀላል ጥገና ወይም ሰርቪስ አገልግሎት በመስጠት ወጪ ከማዳን ባሻገር ተሽከርካሪዎችን በፍጥነት በመጠገን ጊዜ መቆጠብ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም ለ305 ተሽከርካሪዎች የመካከለኛና ከባድ ጥገና አገልግሎት እንዲሁም ለ10 ተሽከርካሪዎች የሞተር ዕድሳት መደረጉንም ነው አቶ ብሩክ የተናገሩት፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል ጋራዥ የሞተር ዕድሳት፣የቦዲ ዕድሳትና የቀላል ጥገና አገልግሎቶች እየሰጠ እንደሚገኝ አቶ ብሩክ አስታውቀዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

3 × four =