የተቋሙ የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ በይፋ ተመረቀ

Published by corporate communication on

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል  ዋና  መሰሪያ ቤት የተገነባው የህፃናት የቀን  ማቆያ ማዕከል/ Children Day Care Center/ ዛሬ  በይፋ ተመረቀ፡፡

ማዕከሉን በይፋ የመረቁት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ  አቶ አሸብር ባልቻ  እንደተናገሩት የተቋሙ ሴት ሠራተኞች በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ የማዕከሉ መገንባት ከፍተኛ እገዛ ያድርጋል፡፡

በቀጣይም ለማዕከሉ የሚያስፈልጉ ቀሪ ግብዓቶችን በአፋጣኝ አሟልቶ በቅርቡ  ሥራ ለማስጀመር ትኩረት ተሰጥቶት  እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል  የሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት  ጉዳይ መምሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ  በበኩላቸው እንደገለፁት ሴት ሠራተኞች ከወሊድ በኋላ ወደ ስራ ገበታቸው ሲመለሱ ስራቸውን በትጋት እንዲሰሩ እና በልጆቻቸው ምክንያት ከስራ ገበታቸው እንዳይቀሩና  እንዳያረፍዱ ያግዛል፡፡

ሠራተኞቹ  የልጆቻቸን ጤናና ደህንነትለመከታተልም የህፃናት ማቆያ ማዕከሉ አይተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል፡፡

ማእከሉ ዕድሚያቸው  ከ6 ወር አስከ አራት ዓመት የሚደርሱ ከአርባ  እስከ ሃምሳ የሚሆኑ  ህጻናትን ተቀብሎ የማስተናገድ አቅም እንዳለው የጠቆሙት ዳይሬክተሯ በሚቀጥለው ሳምንት በጊዚያዊነት ስምንት ህጻናትን ተቀብሎ ስራ እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡

ግንባታውን በኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ ኃይል የራስ አቅም  የስራ ክፍል ማከናወኑ ተገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የስራ መሪዎች  ‹‹ለሥርዓተ-ጾታ እኩልነት የመሪዎች ሚና ›› በሚል ርዕስ የፓናል ወይይት  በዛሬው ዕለት አካሂደዋል ፡፡

የፓናል ውይይቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሴቶች፣  ወጣቶችና ህፃናት  ጉዳይ መምሪያ ከኢትዮጵያ ሴቶች የኢነርጂ ባለሙያዎች ማህበር (Ethiopian woman in energy association ) ጋር በመተባበር  መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል  የሴቶች፣  ወጣቶችና ህፃናት  ጉዳይ  መምሪያ ዳይሬክተር  ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ  እንደተናገሩት  በተቋሙ  በአሁኑ ወቀት  በሥርዓተ-ጾታ እኩልነት  ዙሪያ ያለውን ክፍተት  በመለየት እና መፍትሄ ለማምጣት የከፍተኛ የስራ  መሪዎች  ሚና ወሳኝ በመሆኑ ይህ የውይይት  መድረክ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች የኢነርጂ ባለሙያዎች ማህበር ተጠባባቂ ፕሬዜዳንት ወ/ሮ ልእልና ክፍሌ በበኩላቸው የውይይት መድረኩ  የሥርዓተ- ጾታ እኩልነት  ለማረጋገጥ የስራ መሪዎች ሚና ምንመሆን እንዳለበት የሚጠቁምና ችግሮችን ለመቅረፍ ምን መስራት ይገባል የሚለውንላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ይረዳል ብለዋል፡፡

በፓናል ወይይቱ  ላይ ተቋሙ በሥርዓተ-ጾታ እኩልነት ዙሪያ እየሰራቸው ያሉ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

በመድረኩ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ  መሪዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ህግ ሴቶች ማህበር ፣የዓለም ባንክ እና የኢትዮጵያ ሴቶች የኢነርጂ ባለሙያዎች ማህበር ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

fourteen − 1 =