የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የኢትዮጵያዊነት ቀንን አክብረዋል
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስራ መሪዎችና ሠራተኞች የኢትዮጵያዊነት ቀንን በተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ አክብረዋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2013 ዓ.ም የጳጉሜ ቀናቶች በተለያዩ ስያሜዎች እንዲከበሩ በወሰነው መሰረት የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞችም የኢትዮጵያዊነት ቀን የሚል ስያሜ የተሠጠውን ጳጉሜ 1 ቀንን አክብረዋል፡፡
የኢትዮጵያን አንድነትና ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ጀግኖች አባቶቻችን ደማቸውን ያፈሰሱላትንና አጥንታቸውን የከሰከሱላትን ኢትዮጵያን እንደሀገር ለማስቀጠል፤ ሉዓላዊነቷን ለማስከበርና ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ ለማድረግ በተለያየ መልኩ በቁርጠኝነት በመሰለፍ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መንቀሳቀስ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል፡፡
ኢትዮጵያዊ ሁሉ በኢትዮጵያዊነቱ እንደሚኮራው ሁሉ ሀገርም ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ትልቅ ኃላፊነት ስለምትጠብቅ ሁሉም በተመደበበት የስራ መስክ ላይ በትጋትና በቅንነት በማገልገል ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል፡፡
የ2013 ዓ.ም የጳጉሜ ቀናቶች የኢትዮጵያን ባህልና ትውፊት በሚያሳድጉ መልኩ በተለያዩ ስያሜዎች የሚከበሩ ሲሆን ቀናቶቹ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊነትንና የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በሚያጠናክር መልኩ ሲከበሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡
0 Comments