የቡኢ ባለ 132/33/15 ኪ.ቮ. እና የነጆ ባለ 132/33 ኪ.ቮ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በቅርቡ በይፋ ተመርቀው ሥራ ይጀምራሉ

Published by corporate communication on

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ እና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት  በምዕራብ ወለጋ ዞን  ነጆ ከተማ የተገነቡት የማከፋፈያ ጣቢያዎች በይፋ ተመርቀው ሥራ ሊጀምሩ ነው፡፡

የቡኢ ባለ 132/33/15 ማከፋፋያ ጣቢያ  አራት ባለ 15 ኪ.ቮ እና አራት ባለ 33 ኪ.ቮ ወጪ መስመሮች እንዲሁም 50 ሜጋ ቮልት አምፒር  አቅም ያለው ትራንስፎርመር  አለው፡፡

ለማከፋፈያ ጣቢያው ከቡታጅራ ነባር የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተነስቶ ቡኢ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ  30 ኪ.ሜ የሚረዝምና 78 የኃይል ተሸካሚ ማማዎች የተተከሉለት ባለ 132 ኪ.ቮ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል፡፡

በተያያዘ ዜና እና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን  ነጆ ከተማ የተገነባው ባለ 132/33 የማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡

ከአዲስ አበባ በ500 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ተገንብቶ ለምርቃት ዝግጁ የሆነው የነጆ ማከፋፈያ ጣቢያ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር  ትራንስፎርመር እና አራት ባለ 33 ኪ.ቮ. ወጪ መስመሮች አሉት፡፡

ለማከፋፈያ ጣቢያው ከጊንቢ – መንዲ ከተዘረጋ ባለ 132  ኪ ቮ. መስመር  ላይ ተቆረጦ የሁለት ኪ.ሜ  ርዝመት ያለው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተዘርግቷል፡፡

ሁለቱ የማከፋፈያ ጣቢያዎች በቡኢ እና በነጆ ከተሞችና በዙሪያቸው ላሉ አካባቢዎች አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያስችላሉ ተብሎ ይታመናል፡፡

የማከፋፈያ ጣቢያዎቹን ገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ያደረገው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  ኃይል የትራንስሚሽንና  ሰብስቴሽን ኮንስትራክሽን የራስ አቅም(Own force ) ቢሮ ነው፡፡ 

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

one × 2 =