የቅድመ ኃይል ማመንጫ ዩኒቶች የኮንክሪት ሙሌት ስራ ጀመረ

Published by corporate communication on

 ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ የኒቶች መካከል ቅድሚያ ኃይል የሚያመነጩት ዩኒት 9 እና የዩኒት 10 ማዕከላዊ ክፍል የስቲል ስትራክቸር ሥራዎች በማለቃቸው የኮንክሪት ሙሌት ስራ መጀመሩ በምክትል ስራ አስኪያጅ የህዳሴ ግድብ ፕሮጅክት ሳይት አስተባባሪ አቶ በላቸው ካሳ ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩት የኤሌክትሮ ሚካኒካልና ኃይድሮ ስቲል ስትራክቸር ስራዎች በሚፈለገው ጥራትና ወቅት ሥራዎቹን ማከናወን ባለመቻሉ ለሲቪል ሥራው መዘግየት እንደ አብይ ምክንያት መወሰዱ ይታወሳል፡፡

በቅርቡ በተደረገው የማሻሻያ እርምጃ መሰረት የስቲል ስትራክቸር ሥራዎችን ለቻይናው ሲጂጂሲ ካምፓኒ ከተሰጠ በኋላ ስራው እየተፋጠነ ይገኛል፡፡ በተለይም የዩኒት 9 እና 10 በዝቅተኛው የግድብ ከፍታ  ቀድመው ኃይል እንዲያመነጩ ለማስቻል የግድቡን ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ ወደ 560 ሜትር ለማድረስ  የኮንክሪት ሙሌት ስራ መጀመሩን አቶ በላቸው ተናረዋል፡፡

ቀድሞ ተሰርቶ የነበረው የግድቡ የውሃ መስተፈሻ (Bottom outlet) ስቲል ስትራክቸር ሥራ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ አለመሆኑ በባለሙያዎች በመረጋገጡ የውሃ መስተፈሻ እና ቀሪ ዩኒት 9 እና 10 የስቲል ስትራክቸር ዕቃዎች እንደገና በቻይና እንዲመረት ተደርጎ ወደ ሳይቱ ቦታ ተገጓጉዘዟል፡፡

እስከ አሁን 27 ትራክ መኪናዎች ወደ ሳይቱ በመድረሳቸው የውሃ ማስተንፈሻ ስቲል ስትራክቸር የተከላ ሥራ ተጀምሯል፡፡ ቀሪዎቹም እቃዎች ጂቡቲ ወደብ ደርሰዋል፡፡ 

ከውሃ ማስተፈሻ (Bottom outlet) በስተግራ በኩል 26 ሺህ ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሌት የተከናወነ ሲሆን በስተ ቀኝ በኩል ደግሞ የ50 ሺህ ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ከ14/01/2012 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በአሁኑም ወቅት ቀድሞ ያመነጫል ተብሎ ለሚታሰበው ለዩኒት ዘጠኝ ማዕከላዊ ሴክሽን የግንባታ ክፍል ከሚያስፈልገው 1552 ነጥብ 8 ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ሙሌት ውሰጥ በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 665 ነጥብ 7 ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ተከናውኗል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

3 + five =