የሱልልታ -ደብረ ማርቆስ መስመር የጥገና ሥራ በብሔራዊ ግሪድ ላይ የጎላ ተጽዕኖ ሳያሳድር እየተገባደደ ነው

የሱልልታ -ደብረ ማርቆስ ባለ 400 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የጥገና ሥራ በብሔራዊ የኃይል ቋት ወይም ግሪድ ላይ የጎላ ተጽዕኖ ሳያሳድር እየተገባደደ ነው።
ከማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጥገናው እየተከናወነ የሚገኘው የሱልልታ -ደብረ ማርቆስ _ ባህርዳር መስመር እና የምሰሶ ጥገና ሥራ በተያዘለት መርሃግብር መሰረት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በጥገና ሥራው የተነሳ በግሪድ ላይ የደረሰው ጫና ከ 4 በመቶ ያልበለጠ መሆኑን ከቀናት በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡
የተጀመረው እና 5 ቀኑን ያስቆጠረው የጥገና ሥራን በ7 ቀን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
በአሁኑ ሰዓት በመሬት መንሸራተት ምክንያት የተጎዱ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎችን መልሶ የመትከል ሥራው የተጠናቀቀ ሲሆን የመስመር ዝርጋታና የማገናኘት ሥራ እየተሰራ ነው።
የጥገና ሥራውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የራስ ኃይል የኮንስትራክሽን ቢሮ ሲሆን ቢሮው አዳዲስ የማከፋፈያ ጣቢያና ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቶችን ከመገንባት ጀምሮ የጥገና ሥራዎችን ይገኛል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከሱሉልታ – ደብረ ማርቆስ በተዘረጋው ባለ 400 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች በአባይ ሸለቆ እና በአዋበል ወረዳ ሉማሜ ከተማ አካባቢ በመሬት መንሸራተት የተነሳ መጎዳታቸው የሚታወስ ነው።
0 Comments