የሰኮሩ እና የጅማ 2 ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የኃይል ስርጭት በማሳለጥ ደረጃ ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ ናቸው

Published by corporate communication on

የሰኮሩ ባለ 400 ኪ.ቮ እና የጅማ 2 ባለ 230 ኪ.ቮ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን የኃይል ስርጭት በማሳለጥ በኩል ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ መሆናቸውን የጣቢያዎቹ ሥራ አስኪያጆች አስታውቀዋል፡፡

የሰኮሩ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ አንድነት ማሞ እንደተናገሩት የሰኮሩ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በሀገሪቱ ካሉ ግዙፍ ጣቢያዎች አንዱ መሆኑንና በአማካኝ 120 ሜጋ ዋት ኢነርጂ የመሸከምና ማስተላለፍ አቅም ያለው ነው፡፡

ጣቢያው ለወልቂጤ፣ ለጅማ፣ በደሌ፣ ሚዛን፣ መቱ፣ ጋምቤላ፣ ነቀምት እና በአቅራቢው ለሚገኙ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አውታሮችን በማንቀሳቀስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡

እንደ አቶ አንድነት ገለፃ ጣቢያው ሶስት ወጪ መስመሮች ያሉት ሲሆን ለጌዶ፣ ወልቂጤና ጂማ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች 230 ኪ.ቮ ኢነርጂ በማቅረብ ላይ ነው፡፡

በሌላ በኩል በ2007 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት የጀመረው የጂማ ቁጥር 2 ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለጂማ ዩኒቨርሲቲ፣ ለሰርቦ ፣ለጂማ ውሃ አገልግሎት እና ለቆጪ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ከፍተኛ አስተዋጽኢ እያበረከተ መሆኑንን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ይልማ አበበ ገልፀዋል፡፡

አንድ ፓወር ትራንስፎርመርና ሁለት አውቶ ትራንስፎርመር ያሉት ይህ ጣቢያ ለአጋሮ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ 230 ኪ.ቮ፣ ለጂማ ቁጥር 1 እና ለአባ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ደግሞ 132 ኪ.ቮ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ነው አቶ ይልማ የተናገሩት፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

three × 3 =