የሥርዓተ -ጾታ እኩልነትን በሁሉም የስራ ክፍሎች ለማስፋፋትና ለመተግበር እየተሰራ ነው

Published by corporate communication on

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  ኃይል ሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ  የስርዓተ -ጾታ  እኩልነትን በሁሉም የኃይል ማመንጫዎች፣ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና በሪጅኖች ለማስፋፋት እና ለመተግበር  የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡

ቢሮው በሥርዓተ-ጾታ ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ  ከኃይል ማመንጫ፣ ከማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ከሪጅኖች ለተወጣጡ የሴቶች ፣ህጻናት እና ወጣቶች  ጉዳይ ተወካዮች በዋናው መስሪያ ቤት አዳራሽ ለሁለት ቀናት የሰጠው የግንዛቤ  ማስጨበጫ ስልጠና እና ውይይት ዛሬ ተጠናቋል፡፡

በስልጠናው ላይ የቢሮው  ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ አደኤ እንደተናገሩት የስልጠናው ዋና ዓላማ የስርዓተ -ጾታ እኩልነትን በማረጋገጥ  የሴቶችን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት እንዲሁም በህጻናት ደህንነት  በሁሉም የስራ ክፍሎች ለማስጠበቅ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው፡፡

ሠልጣኞች በጽንሰ ሃሰብ እና በልምድ ያዳበሩትን  እውቀት በአግባቡ በመጠቀም  ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ዳይሬክተሯ አስገንዝበዋል ፡፡

በቢሮው የሥርዓተ ጾታ ባለሞያ አቶ ተስፋዩ ዮሀንስ በበኩላቸው  ስልጠናው  ከቢሮው ጋር በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ለመስራት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ 

የስልጠናው ተሳታፊዎች በየስራ ክፍላቸው ባሉ የተለያዩ መዋቅሮች በመታቀፍ የሴቶች ፣የህጻናትና ወጣቶች መብትና እና ጥቅማ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ ያግዛቸዋል  ብለዋል ፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

nineteen + 17 =