የሥራ ዘርፉ የመጀመሪያውን የሩብ በጀት ዓመት ግምገማ አካሄደ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስሚሽን ሰብስትሽን ኦፕሬሽን የስራ ዘርፍ የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማው ውይይት ላለፉት ሁለት ቀናት በአዋሳ ከተማ አካሄደ፡፡
በግምገማዊ ውይይቱ ላይ ትራንስሚሽን ሰብስትሽን ኦፕሬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ሐብታሙ ውቤ፣የትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን የሰርቪስ ዳሬክተር አቶ አስማኤል ሙዘይን፣ከሰሜን ሪጅን በስተቀር የሁሉም ሪጂኖች እና ንኡስ ሪጂኖች ዳሬክተሮች ፣ የትራንስሚሽን ሰብስትሽን እና የጄኔሬሽን ኦፕሬሽን የስው ኃይል ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት አማን እና የየሪጂኖቹ የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስኪያጆች እንዲሁም ከፍተኛ ባለሞያዎች ፣የብሄራዊ ኃይል መቆጣጠሪያ የስራ ሃላፊዎች እና የመስረታዊ ስራተኞች ማህበር ሊቀ መንበር አቶ መኮንን ክፍሌ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ትራንስሚሽን ሰብስትሽን ኦፕሬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ሐብታሙ ውቤ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የስራ ዘርፉን የውጤት ተኮር የስራ አፈጻጸም ምዘና ስርዓት ትግበራን በተቀናጀ እና በተናበበ መልኩ ለመተግበር ከሪጅን ዳይሬክተሮች እና ከዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የዘርፉን የቁልፍ አፈጻጸም መለኪያ(KPI ) አቅድ ግዜ ተሰጥቶት በማዘጋጀት እና በውጤት ተኮር ስርዓት አካተን በመተግበራችን ከምንግዜውም የተሸለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የሥራ ዘርፉ የ2014 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የ KPI አፈጻጸም 98.22 በመቶ የደረሰ ሲሆን ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ የሩብ በጀት ዓመት ከተመዘገበው የ14.02 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተነግሯል፡፡
የዚህ ግምገማዊ ወይይት ዋና ዓላማም በውጤት ተኮር የ KPI ምዝና ትግበራ ወቅት ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ ለማጠናከር፣የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ እንዲታረሙ አቅጣጫ የማስቀመጥ፣የልምድ ልውውጥ እና መልካም ተሞክሮን የማካፍል ፣የተሸለ አፈጻጸም ያመጣውን ሪጀን እውቅና በመስጠት የውድድር ስርዓቱን ጥበልት የማጠናከር ፣ የርስ በርስ ግንኙነት እንዲጠናከር ምቹ ሁኔታን መፍጠር እና ማከፍፈያ ጣቢያዎች ላይ የመስክ ምልከታ ጉብኝት ማካሄድ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ትላንት በተጠናቀቀው እና ለሁለት ቀናት በቆየው ግምገማዊ ውይይት ሪጂኖቹ በቀረቡት ስድስት የ KPI መለኪያ ውጤት አንጻር የታየባቸውን ክፍተቶች በግልጽ በመወያትና በመገማገም የመፍተሄ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡በቀጣይም ድክመቶቹ ተስተካክለው እንዲመጡ የጋረ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በሩብ በጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገበው የደቡብ ምእራብ ሪጅን እውቅና ተሰጥቷል፡፡
0 Comments