የሚዛን ማከፋፈያ ጣቢያ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል

Published by corporate communication on

ከአዲስ አበባ በ561 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን በሚዛን ከተማ የሚገኘው የሚዛን 132/66/33/15 ኪ.ቮ. ከፍተኛ ማከፋፈያ ጣቢያ ተገቢውን አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡

የጣቢያው ተወካይ ኃላፊ ወ/ት ታደለች ተረፈ እንደተናገሩት በ1998 ዓ.ም. ከቦንጋ ማከፋፈያ ጣቢያ 132 ኪ.ቮ. በመቀበል ለሚዛን ከተማና ለአካባቢው በ15 እና 33 ኪ.ቮ. ወጪ መስመሮች ኃይል በመስጠት በይፋ ሥራ የጀመረው ጣቢያው አገልግሎቱን ሳያቋርጥ እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

እንደተወካይ ኃላፊዋ ገለፃ ማከፋፈያ ጣቢያው በ15 ኪ.ቮ ወጪ መስመር ለሚዛን ከተማ ፣ ለሸኮ ወረዳ እና ለአካባቢው ሃይል ሲሰጥ በ 33 ኪ.ቮ ወጪ መስመሮች ደግሞ ለጨና፣ ለዲማ ወረዳዎች እና ለአካባቢው ኃይል በማቅረብ የሚጠበቅበትን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ማከፋፈያ ጣቢያው በደቡብ ምዕራብ ሪጅን ስር ካሉት 14 ማከፋፈያ ጣቢያዎች መካከል ከኃላፊነት ጀምሮ የሴቶች ሚና ጎልቶ የሚታየበትና የጣቢያው ኃላፊን ጨምሮ ሁለት ኦፕሬተሮች ሴቶች የሚገኙበት ነው፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

4 × three =