የመቀሌ-ዳሎል የኃይልፕሮጀክት ግንባታ በተያዘለት መርሃ ግብር እየተከናወነ ነው

Published by corporate communication on

ህዳር 2011ዓ.ም ግንባታው በይፋ የተጀመረው የመቀሌ ዳሎል ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያና ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክትን በተያዘለት መርሃ ግብር ለማጠናቅቀ የግንባታ ስራው በመፋጠን ላይ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ ከነባሩ የመቀሌ 230 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ አንስቶ እስከ ዳሎል 230/132 ኪ ቮ. የኃይል ማከፋፍያ ጣቢያ የሚደርስ ነው፡፡

ርዝመቱ 130ኪ.ሜ የሚሸፍን የ230 ኪ.ቮጥምር ሰርኪዩት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታያካተተ ነው፡፡

በነባሩ የመቀሌ 230 ኪ.ቮ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ስራ እና በዳሎል ባለ 230/132 ኪ.ቮ.አዲስ የጂ.አይ.ኤስ የኃይል የማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ስራዎችን የሚያጠቃልል ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ሳይት ሲቪል መሀንዲስ አቶ ዳዊትይብጌታእንደተናገሩት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታው 316 የብረት ማማዎች የሚያስፈልጉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ የ215 ማማዎች የመሰረት ግንባታእና የ87 ማማዎች የተከላ ስራዎች ተከናውኗል፡፡

በቀጣይም ቀሪዎቹን የመስመር ዝርጋታ ስራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ከመቀሌ ከተማ በ170 ርቀት ላይ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዳሎል ወረዳ እየተገነባ የሚገኘው አዲስ ባለ 230/132 ኪ.ቮ.ከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ግንባታ ስራ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡

400 በ400 ሜትር ካሬ ስፋት ላይ የሚገኘው የዳሎል ማከፋፍያ ጣቢያ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የመሰረት ቁፋሮ እና ግንባታዎች እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ግንባታው የአካባቢውን ከፍተኛ የአየር ሙቀትለመቋቋም እንዲያስችለው በጂ.አይ.ኤስሲስተም (ጋዝ ኢንሱሌትድ ሲስተም) በሚይዝ ቴክኖሎጂ የሚገነባ ነው፡፡

ግንባታውን በ18 ወራት ውስጥ አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ሲሆን የፕሮጀክቱ አማካይ የስራ አፈጻጸም ከ48 በመቶ በላይ መድረሱተ ገልጿል፡፡

የዚህን ፕሮጀክት የመስመር ዝርጋት ካልፓታሩ እንዲሁም የማከፍፍያ ጣቢያ ግንባታውን ላርስን ኤንድ ቱርቦ የተባሉ የህንድ ኩባንያዎች እንዲያከናውኑ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦለታል፡፡

ከተመደበው ፋይናንስ ውስጥ 85 በመቶው ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ ብድር እናቀሪው 15 በመቶ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፍንይሆናል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት በዋና አማካሪት ላማየር የተባለ የጀርመን ኩባንያ እና በረዳትነት ደግሞ ኢኮም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ እንዲሁም የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ክፍል ስራውን በበላይነት በመቆጣጠር ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በዋናነት በዳሎል አካባቢው የሚገኘውን ፖታሸ ለማምረት እና በአካባቢው ለሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ኃይል በአስተማማኝ ሁኔታ ለማቅረብ የሚያስችል ይሆናል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

8 + one =