የህዳሴ ግድብ የታችኛው የውሃ ማስተንፈሻዎች ተጠናቀው ስራ ጀመሩ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የታችኛው የውሃ ማስተንፈሻ ሁለት ቱቦዎች(Bottom outlet) ተጠናቅቀው ሥራ የሙከራ ሥራ ጀምረዋል፡፡
የውሃ ማስተንፈሻዎቹ የዓባይን ወንዝ አጠቃላይ ዓመታዊ የውሃ ፍሰት መጥነው የማሳለፍ አቅም እንዳላቸው የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ገልፀዋል፡፡
የውሃ ማስተንፈሻዎቹ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት በዓመት በአማካይ የሚያገኙትን የውሃ ፍሰት እንደማያስተጓጎል ማረጋገጫ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡
ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ከመከናወኑ በፊት በተጠናቀቁት የውሃ ማስተንፈሻዎች አማካኝነት ተጨማሪ ውሃ እንደምትለቅ እና መረጃም እንደምታጋራ ገልፀዋል።
0 Comments