የህልውና ዘመቻውን ለሚቀላቀሉ የተቋሙ ሠራተኞች ሽኝት ተደረገ

Published by corporate communication on

በሀገራችን እየተካሄደ የሚገኘውን የህልውና ዘመቻ ለሚቀላቀሉ ሁለተኛ ዙር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ሽኝት ተደረገላቸው፡፡

በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ  አስፈጻሚ  አቶ አሸብር ባልቻ በአሸባሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን እየተሰነዘረ ያለውን ሀገር የማፍረስ አደጋ ለመቀልበስ ተቋሙን ወክለው ለሚዘምቱ ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሥራ አስፈጻሚው ሠራተኞች ዘመቻውን በፅናትና በአሸናፊነት ተወጥተው ወደ መደበኛ ሥራቸው እንደሚመለሱም እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

የዋና ሥራ አስፈጻሚ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝ በበኩላቸው ጀግኖች አባቶቻችን ከውጭ ወራሪ ጠብቀው ያቆዩዋትን ሀገር በመካድ ጥቃት እያደረሰ የሚገኘውን የህወሓት ከሃዲ  ቡድን ለመደምሰስ ተቋሙ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አንስተዋል፡፡

ከድጋፉ በተጨማሪ ዘመቻውን በአካል ተቀላቅሎ አሸባሪ ቡድኑን ለመፋለም ፍላጎት ላላቸው 6 የተቋሙ ሠራተኞች ሽኝት መደረጉን የተናገሩት አቶ ሙላት 3 ሠራተኞች ቀደም ብለው ዘመቻውን መቀላቀላቸውን ገልፀዋል፡፡

ሰራተኞቹ በተቋሙ የነበራቸውን ተሳትፎ በህልውና ዘመቻው በመድገም ተቋማቸውን እና ሀገራቸውን እንደሚያኮሩ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

ሽኝት የተደረገላቸው ሠራተኞች አሸባሪውን ቡድን ለመከላከልና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት በሚደረገው ዘመቻ ለመሳተፍ ያነሱት ጥያቄ በተቋሙ ተቀባይነት አግኝቶ በክብር ሽኝት መደረጉ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡ 

ዘማቾቹ ሀገር ከሁሉም በላይ መሆኗን በማንሳት ሥራም ሆነ ህይወት ሊቀጥሉ የሚችሉት ሀገር ሲኖርና  ሰላም  ሲሆን ብቻ ነው ብለዋል፡፡ 

በዘመቻው እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ወታደር መሆኑን ተገንዝቦ ለሚደረግለት ማንኛውም ጥሪ መዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

three × 2 =